"የኔ" የምላትን

2 years ago
1

የኔ የምላትን

(ቱካ ማቲዎስ)

በሚነፍሱ ተጓዥ ነፋሣት
                    እረፍት አልባ ደመናት
በሰማይ በጥልቁ ህዋ
ይዤሀለሁ ማናት ግን የኔዋ?
                     በማህበል ግጭት
           አረፋ ኩርፊያ
በባህሩ ሞገድ
        እጥፋት ልፊያ
በበራሪ ክዋክብት ሩጫ
በፀሐይ ምህዋር አቅጣጫ
በአሥደናቂ ነፀብራቋ
አይን አጥበርባሪ ሣቋ

ይዤሀለሁ....

ፍቅሬን አምጣልኝ
ፀሎቴንም ስማኝ

በቁራ ጥልቅ ጩህኸት
በንሥር ርቆ በራሪ አክናፋት

ባለረጃጅም እግሯ........ወፍ አቋቋም
እሥክትሠማኝ ዝንተ አለም ልቁም ግዴለም

እንደ ስለታም ቋጥኝ ዝምታ
እንደ መንጋ ጒሽ ጋጋታ

ሆኜ ልለምንህ....

ፍቅሬን አምጣልኝ
ፀሎቴንም ሥማኝ

እንደ ረጅም ጥልቅ ጥላ
ቀትር እንደሚያጠላ

እንደ አጥቢያ ኮከብ ድምቀት
እንደ ፅልመቱ ጥቁረት

እንደ ክረምት ሞቃት ፀሐይ
አለሜን እንዳይ

ፍቅሬን አምጣልኝ
ፀሎቴንም ሥማኝ

በፅጌረዳ መሀዛ
ህይወቴ እንዲወዛ

እንደ ከርቤ ብርጉድ
የከበረ ልቤን ላዥጒድጉድ

እንደ ዘማሪ ወፍ ቅኝት
እንደ አናብስት ማጓራት

እንደ ጅብ ላሽካካ
በለኝ ይህው ውሰዳት እንካ

ፀጥ እንዳለው አየር ድምፅ
እንደ ፏፏቴ ጩኸት ላምፅ

እንደ ሴት ሣቅ
በደሥታዬ አልሣቀቅ

በእሣት እንደሚነድ

ደረቅ እንጨት
አቅሌን አልሣት

እንደ እሣተ ገሞራ እቶን
የምሽት ሻማ ብርሀን
አልንደድ ብቻዬን

በሚወዱት እጅ እንደመዳሰስ
በከናፍር እንደ መሳም በስሰ

እንደ አፍላ ወጣት ፍቅር
ሕይወቴም እንዲሁ ይቀየር

እንደ ምሽቱ ፀጥታ
የበሰለ አእምሮ እርጋታ

ደሥ እንደሚያሰኝ ጥልቅ እንቅልፍ
አብሬያት ልክነፍ

ይሄን ሥልህ...

በልቤ ምት ጥልቀት
መኖሬን በምቆጥርበት

እምላለሁ
እ.ፈ.ል.ጋ.ታ.ለ.ሁ

ፍቅሬን አምጣልኝ
ፀሎቴንም ሥማኝ

አሜን!

(ነፅሩ ወዘሰናየ አፅንሁ)

Loading comments...