Premium Only Content
መላዕክት ማለት ምን ማለት ነው?
ቅዱሳን መላእክት
ቅዱሳን መላእክት ከተፈጠሩባት ከመጀመሪያዋ እለተ እሁድ አንስቶ እስከ ዛሬ ወደ ፊት ለዘለዓለም እግዚአብሔርን በቅድስና የሚያገለግሉ ተፈጥሯቸው የተቀደሰ ሕይወታቸውም በንጽሕና የተሞላ ነው፡፡
ቅዱሳን መላእክት በመንፈሳዊ ዓለም እየኖሩ በሰማይና በምድር በእግዚአብሔርና በሰው ፊት የቅድስናን መንፈሳዊ ሥራ የሚሰሩ ረቂቅ ፍጡራን ናቸው፡፡
መላእክት ማለት ምን ማለት ነው?
መልአክ የሚለው ቃል
<<ለአከ>> ከሚለው የግዕዝ ቃል የተገኘ ሲሆን
<<ለአከ>> ማለት ላከ ወይም ሰደደ
ማለት ነው።
መልአክ የሚለው ቃል
<<በቁሙ የእግዜር መልዕክተኛ
ሰማያዊ፣ረቂቅ፣የእሁድ ፍጥረት>> የሚል ትርጉምን ይሰጠናል።
አንድም
መልአክ የሚለው ቃል<< አለቃ፣ሹም፣አበጋዝ፣ተሹሞ ከንጉስ
የተላከን>>ያመላክታል።
መላእክት የቃሉ ትርጉም
መላእክት የሚለው ቃል በ3 መንገድ ሊተረጐም ይችላል፡፡
1 መላእክት
<<መላዕክት>> ማለት
መልእክተኞች፣ ተላላኪዎች ማለት ነው፡፡
ይህን ተግባር የሚፈፅሙት ቅዱሳን ሰማያውያን መላእክት ናቸው፡፡ የእርቅ፣የሰላም፣የበረከት መልእክተኞች ናቸውና፡፡
2 መላእክት
<<መላእክት>> ማለት አለቆች፣ገዢዎች ማለት ነው፡፡
ይህ ደግሞ በሥልጣን መንበር ላይ ላሉ ሰዎችና ለቤተክርስቲያን አስተዳዳሪዎች አለቆች የሚሰጥ ስያሜ ነው፡፡
ራዕይ ዮሐ፦1፥20
<<በቀኝ እጄ ያየሃቸው የሰባቱ ከዋክብትና የሰባቱ የወርቅ መቅረዞች ምስጢር ይህ ነው፡፡ ሰባቱ ከዋክብት የሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት መላእክት ናቸው፣ ሰባቱም መቅረዞች ሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት ናቸው>> እንዲል፡፡
መልአከ አርያም፣መልአከ ሰላም፣መልአከ ገነት እንደሚባለው አጠራር ነው።
3 መላእክት
<<መላእክት>> ማለት ከክብር ይልቅ ኃሣርን መርጠው የተዋረዱትን ርኩሳን መናፍስት አጋንንትን መላእክት ይላቸዋል፡፡
ማቴ 25 41
<<እናንተ ርጉማን ለሰይጣንና ለመላእክተኞቹ ወደተዘጋጀ ወደዘለዓለም እሳት ከእኔ ሄዱ>> እንዲል፡፡
መላእክት የሚለው ቃል ሲተነተን
መ
መገብት(መጋብያን)የሚመግቡ
ከመላእክት አገልግሎትና ተልእኮ መካከል የሰውን ልጅ ለቁመተ ስጋ የሚሆን ምግብን መመገብ አንዱ ነው፡፡ይህም በመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ተጽፎ እናገኘዋለን፡፡
መጽ.ነገ. ቀዳ፦19፥2-8
ዘጸ 16፥35
መዝ፦77፥24
ቅዱሳን መላዕክት በሰው ላይ ያለውን
ችግር ተረድተው የጎደለውን ያሟላሉ።
መጋቢያ ምስጢር
የእግዚአብሔር ፀጋ የሚመግቡና የሚመክሩ ናቸው።
የእግዚአብሔርን ሕግ የሚሽሩትን
የሚያፈልሱትን ይገስፃሉ፣ይመክራሉ
ያስተምራሉ፣ሕገ እግዚአብሔርን
የሚጠብቁትን ይጠብቃሉ።
ዘፀ፦23፥20
ዘካ፦1፥9
የሐዋ.ሥራ፦27፥23-25
መላእክት ከምግበ ስጋ ባሻገር ምግበ ነፍስ የሆነውንም ጽድቅ ይመግቡናል (ያስተምሩናል) ፡፡
ራዕይ.ዮሐ፦18፥10
ዳን፦10፥21
ላ
ላዕላውያን
መላእክት ሰማያውያን እንደሆኑ የሚያስረዳ ቃል ነው።
ላዕላውያን የሚለው ቃል ሰማያውያን ከሚለው ፍቺው በተጨማሪ በክብር ከፍ ያሉ ልዑላነ ክብር የሚል ፍቺ ይኖረዋል፡፡ይህም ፍቺ በበለጠ ክቡራን ከሚለው ቃል ፍቺ ጋር የሚወራረስ ነው።
ማቴ፦24፥36
ማቴ፦22፥30
መላእክት ንፁሀን፣ክቡራን
የእግዚአብሔር አገልጋዮች ስለሆኑ
ከሰዎች በላይ ሆነው ያገለግላሉ
ልመናችንንና ጸሎታችንን ወደ እግዚአብሔር ስለሚያደርሱ አማላጆቻችን ናቸው።
ሐዋ.ሥራ፦10፥4
ሉቃ፦15፥10
ጦቢ፦12፥15
እ
እቁባነ ምሕረት
የቃሉ ፍቺ በምሕረት የሚጠብቁ የሚል ሲሆን መላእክት ዑቃቤ (ጠባቂ) በመባል ይታወቃሉ፡፡
የመላእክት አገልግሎት ሰውን መጠበቅ ከመከራ ከችግር ማዳን ነው።
ዕብ፦1፥14
ቅዱሳን መላዕክት አምላካችን ልዑል እግዚአብሔር ለሰዎች በሚያደርገው
ምህረትና ቸርነት ይደሰታሉ።ስለሆነም
ምሕረትና ቸርነትን ለሰዎች በፍጥነት ይደርሳሉ።
ክ
ክቡራን
መላእክት ክቡራን ይባላሉ፡፡
ቅዱሳን መላዕክት በአእምሮአቸው ተዕቢት
የሌለባቸው ትሑታንና ቅዱሳን ናቸው እንጂ።
ራዕይ.ዮሐ፦18፥1
ዘፀ፦22 የበለዓም ታሪክ
ቅዱሳን መላዕክት በአእምሮአቸው ትዕቢት
የለባቸውም ትሑታንና ቅዱሳን ናቸው እንጂ።
ዘሌ፦11፥44
ዘሌ፦19፥2
1ኛ ጴጥ፦1፥15-16
ዘፍ፦19፥1
ት
ትጉሃን
መላዕክት ደከመን ሰለቸን የማይሉ፣
ዘወትር ያለማቋረጥ ሀያ አራት ሠዓት ሙሉ <<ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ>> እያሉ እግዚአብሔርን ያመሰግናሉ
ኢሳ፦6
<<እስመ እረፍቶሙ አኮቴቶሙ እስመ አኮቴቶሙ እረፍቶሙ>>
<<እረፍታቸው ምስጋናቸው ምስጋናቸው እረፍታቸው>>እንዲል፡፡
ከዚህ የተነሳ ትጉሃን ይባላሉ፡፡
ከትጉሃን በተጨማሪ ትሁታን ተብሎ ይፈታል
ይሁ፦1፣6
-
52:32
The Dan Bongino Show
3 hours agoProducer's Picks: Bongino's Best Segments - 01/03/25
95.4K309 -
56:49
VSiNLive
2 hours agoA Numbers Game with Gill Alexander | Hour 1
22.1K1 -
LIVE
Film Threat
16 hours ago2025 MOVIES TO LOOK FORWARD TO + JANUARY'S BEST FILMS | Film Threat Livecast
362 watching -
LIVE
The Shannon Joy Show
3 hours ago🔥🔥Friday Freestyle LIVE With Shannon Joy! Ask Me Anything On The Open Live Chat!🔥🔥
334 watching -
LIVE
The Big Mig™
16 hours agoGlobal Finance Forum Powered By Genesis Gold Group
2,060 watching -
1:31:22
Caleb Hammer
2 hours agoEgo-Maniac Thinks She Can Manifest Problems Away | Financial Audit
20.9K1 -
LIVE
LFA TV
5 hours agoSPEAKER VOTE LIVE! | LIVE FROM AMERICA 1.3.25
6,314 watching -
DVR
SpartakusLIVE
4 hours agoDelta Force w/ Phixate || Lord of the Loot secures the JUICE
17.4K1 -
16:49
Dave Portnoy
4 hours agoDavey Day Trader Presented by Kraken - January 3, 2025
32.2K3 -
2:16:11
Matt Kohrs
9 hours agoTesla Falls, Nvidia Bounces & Payday Friday || The MK Show
50.9K5