መዝሙር ደስ ይበለን

4 months ago
93

መዝሙር
ደስ ይበለን እልል በሉ

ደስ ይበለን እልል በሉ/2/
አልቀረም ተቀብሮ ተገኘ መስቀሉ/2/
በብርሐን መላት ዓለምን በሙሉ/2/

ምን ቢተባበሩ ምቀኞች ቢጥሩ/2/
ቅዱስ መስቀሉንም ሸሽገው ቢሰውሩ
/2/
አልቻሉም ሊያጠፉት ምን ቢተባበሩ/2/

በተራራ ተሠውሮ ለዘመናት/2/
ተጥሎ በተንኮል ተደብቆ ከኖረበት/2/
ተገለጠ ዛሬ በመራ እሳት/2/

እሌኒ ናት ይህን ምስጢር ያስገኘችው
/2/
ደመራን በቦታው በጥበብ ያስቆመችው/2/
የተንኮልን ተራራ ያስቆፈረችው/2/

ታሪካዊ የክርስቶስ ህያው መስቀል/2/
ተገለጠ ዛሬ በክብር በግሩም ኃይል/2/
ምን ጊዜም ሲያበራ እንዲህ ይኖራል/2/

Loading comments...