ሆ ብለን መጣን

5 months ago
67

ሆ ብለን መጣን

ሆ ብለን መጣን ሆ ብለን
ሆ ብለን መጣን ሆ ብለን

ቸርነቱን አይተን   ሆ ብለን መጣን ሆ ብለን
ምህረቱን አይተን
አበቦችን ይዘን   
ቄጤ ማውን ይዘን
ቤቶች አሉ ብለን
እሜቴ አሉ ብለን

አበባአየሽ ወይ ለምለም/2/

ስላዘጋጀ             ለምለም
ሰማይ ምድርን    ለምለም
ስለቀመረ           ለምለም
ብርሃናትን           ለምለም
እሱ ነውና           ለምለም
የጊዜ ጌታ           ለምለም
እንዘምርለት        ለምለም
ሆነን በእልልታ    ለምለም
አበባ አሮጌው አልፈፏ አዲስ ተክቷል/2
አበባ ይክበር ይመስገን ይህን አድርጓል/2

አበባአየሽ ወይ ለምለም/2/

ደመናው አልፏል      ለምለም
ፀሐይ ወታለች          ለምለም
መሬት ልምላሜን     ለምለም
ተጎናጽፋለች             ለምለም
አዲሱ ዘመን           ለምለም
አዲሱ አመት           ለምለም
ሰጠን እግዚአብሔር ለምለም
በቸርነት ለምለም
አበባ አሮጌው አልፈፏ አዲስ ተክቷል/2
አበባ ይክበር ይመስገን ይህን አድርጓል/2

አበባአየሽ ወይ ለምለም/2/

የጥፋት ውኃ       ለምለም
የጎደለ ቀን          ለምለም
ለምለሙን አየ     ለምለም
እርግቧን ልከህ    ለምለም
እኛም መተናል     ለምለም
ቄጤማ ይዘን      ለምለም
ሰላም ለናንተ       ለምለም
ይሁን እያልን        ለምለም
አበባ አሮጌው አልፈፏ አዲስ ተክቷል/2
አበባ ይክበር ይመስገን ይህን አድርጓል/2

አበባአየሽ ወይ ለምለም/2/

የሰውን በደል           ለምለም
ይቅር እያለ              ለምለም
እድሜን ለሰው ልጅ  ለምለም
እየቀጠለ                ለምለም
ዘመንን ሽሮ             ለምለም
ዘመን የተካ             ለምለም
እስከ ንስሀ              ለምለም
ይታገሠናል              ለምለም
አበባ አሮጌው አልፈፏ አዲስ ተክቷል/2
አበባ ይክበር ይመስገን ይህን አድርጓል/2

አበባአየሽ ወይ ለምለም/2/

ኢትዮጵያ ትብራ         ለምለም
ትለምልምልን            ለምለም
እጇን ዘርግታ            ለምለም
ወደአምላካችን          ለምለም
የእግዚአብሔር እርሻ  ለምለም
ይሁን ኤፍራታ           ለምለም
እኛም እንጥገብ        ለምለም
ከበረከቷ                  ለምለም
አበባ አሮጌው አልፈፏ አዲስ ተክቷል/2
አበባ ይክበር ይመስገን ይህን አድርጓል/2

አበባአየሽ ወይ ለምለም/2/

ከዘፈን ዓለም             ለምለም
ከእርኩት ስፍራ          ለምለም
ውጡ ከሴኬም          ለምለም
ከሞት ተራራ              ለምለም
ለእግዚአብሔር ይሁን ለምለም
ትንሽ ትልቁ                ለምለም
የጌታን ጥሪ               ለምለም
እንዳትንቁ                  ለምለም

አበባ አሮጌው አልፈፏ አዲስ ተክቷል/2
አበባ ይክበር ይመስገን ይህን አድርጓል/2

አበባአየሽ ወይ ለምለም/2/

አመትን ባመት     ለምለም
ሲተካ ጌታ           ለምለም
ታስሮ የኖረው       ለምለም
ሁሉም ይፈታ       ለምለም
ጰራቅሊጦስም     ለምለም
ይቀድሰን              ለምለም
በአዲሱ መንፈስ   ለምለም
ያመላልሰን           ለምለም

አበባ አሮጌው አልፈፏ አዲስ ተክቷል/2
አበባ ይክበር ይመስገን ይህን አድርጓል/2
አበባአየሽ ወይ ለምለም/2/

ወደ ንስሐ            ለምለም
የሚጠራን            ለምለም
በራችን ቆሟል       ለምለም
አዳኛችን              ለምለም
እንቀበለው           ለምለም
በእምነት ሆነን      ለምለም
እንዳይመለስ        ለምለም
እንዳያልፈን          ለምለም

አበባ አሮጌው አልፈፏ አዲስ ተክቷል/2
አበባ ይክበር ይመስገን ይህን አድርጓል/2

ይሸታል የእጣን ጢስ/2/
ከቤተ መቅደስ/2/

ከብረው ይቆዩን ከብረው/2/
ልቦና መንፈስ ገዝተው
ቃሉን በትጋት ሰምተው
ሥጋና ደሙን በልተው
የፍቅርን ሸማ ለብሰው
ከብረው ይቆዩን ከብረው ።

Loading comments...