ዝክረ ቅዱስ ሚካኤል መንፈሳዊ በጎ አድራጎት(መላኩ) አጀማመሬ

5 months ago
185

ከላይ የቀጠለ፦
ለምሳሌ
-በየፀበል ቦታው በመተትና በድግምት  ሽባ የሆኑ
-በየመንገዱ የሚገኙ ጎዳና ተዳዳሪው
-በየአጥቢያ ቤተክርስቲያኑ ጥግ/ስር የሚገኙ ነድያንን
-አቅመ ደካሞችን
-ወላጅ አልባ ህፃናትን
-አዕምሮ ህሙማን
-የተሰደዱና የሚሰደዱ
-ሥራ አጡ
-ሀብትና ንብረት አፍርተው ሜዳ ላይ
የቀሩ
- በበጎ አድራጎት ተግባር እና ስራ ላይ የተሠማሩ በዓላማ ፀንተው ቆይተው ህዝባቸውን፣ዜጋቸውን ሲረዱ፣ሲታደጉ ሲያገለግሉ የሚገኙ ግለሰቦች ቢጠየቁ
-ወላጅ አልባ ህፃናትን የሚንከባከቡ
-የአዕምሮ ህሙማን የሆኑ እራሳቸውን የሳቱ በተመለከተ የተቋም ሀላፊዎች ቢናገሩ
-በህፃናት እና በሴት እህቶቻችን ላይ ፆታዊ ትንኮሳና የጉልበት ብዝበዛ ቢጠየቅ
-ለገንዘብ ብለው እኔ ገንዘብ አለኝ ምን ታመጣላችሁ እያሉ በሀሰት እየመሰከሩና እያስመሰከሩ እየማሉ ከተወለዱበት፣ካደጉበት ስፍራ የተፈናቁ
-በጎ ስራ የሚሰሩ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ላይ የተለያዪ ሴራዎችን በማሴር ተጎድተው የሚገኙ ቢጠየቁ ወዘተ
-ኸረ ስንቱ ተናግሬና ዘርዝሬ እጨርሰዋለሁ እንዴት እግዚአብሔር እንዳሳዘንን፣ሀገራችንን፣ቤተ ክርስቲያንን እንዳዋረድን፣ምን ያህል እንደተጨካከንን ምን ያህል ከሰውነት ተራ እንደወጣን ቤት ይቁጠረው  በየሰፈራችንና በየመንደራችን የሚገኙ የሰው ፊት ለማየትም ሆነ ለመጠየቅ የተሳናቸው የሚቸገሩ ቁጥራቸው ቀላል አይደለም እኔም ከላይ የጠቀስኳቸውን ወገኖቻችን በመጎብኘት በቅርበት በማነጋገር  ከአንደበታቸው የሚወጣው መልስ ስሰማ ሰው መባልን ያስጠላችኋል የጠላሁበት ነው
እንደዚሁም በነዚህ አባቶች፣እናቶች፣ወንድሞች፣እህቶች ህፃናት ሳይቀሩ ያልተፈፀመ ግፍ፣ወንጀል፣ሰቆቃ፣ሰብአዊ መብት ጥሰት ወዘተ ቀላል ነው የሚባል አይደለም።

እኛ ይህንን ብናውቅ፣ብንረዳ ኖሮ
-ወንድም አህቱ እህት ወንድሙ ላይ ጣቱን ባልቀሰረ ነበር
- ሁሉም ተከባብሮ ተዋዶ ተፋቅሮ ይኖር ነበር
-ከበቀል፣ከጥላቻ፣ከዘረኝነት፣ከጎጥ፣
ከመጠላለፍ አምላኩን እያሰበ እና እየተማፀነ ይኖር ነበር
-እርስ በራስ እየተረዳዳ እና እየተደጋገፈ ሀገሩንም ቤተ ክርስቲያኑንም ይጠብቅ ነበር
-ሁሉም ባለው እውቀት እና ልምድ በተማረበት ስራ ዘርፍ ተሰማርቶ ሀገሩን ባገለገለ ነበር
- እርስ በራስም መገፋፋት እና አንዱ ተሳዳጅ ሌላው ተሳዳጁ ባልነበረ ነበር
- ነገ ጥለነው ለምንሔደው ኮንትራት ዓለም የእግዚአብሔር ሕግ መተላለፋችን ባልዘነጋን ነበር
-ለጥቅም ብለን በወሬና በአሉባልታ፣በቅናትና በምቀኝነት እውነትን ደብቀን በውሸት በህሊናችን ውስጥ ባላነገስን ነበር
- በጎ ነገርን ለሀገራችን፣
ለቤተክርስቲያናችን፣ለህዝባችን መጥቀም ሲገባን እራስ ወዳድነት ባልሆንን ነበር
- ዛሬ አቶ እከሌ ተብለን ወ/ሮ ወ/ሪት እየተባልን እየተጠራን ይህችን ዓለም ተሰናብተን ስንሔድ ግን ሬሳው አስከሬን የሚል መጠሪያ ስም መኖሩን ተዘናግተን እንዲህ መሆናችን ግን በእውነት ያሳዝናል
ያውም በ 21ኛ መ/ክ/ዘ እግዚአብሔር
በምህረቱ ይታረቀን ይጎብኘን እላለሁ።

እኔም ይህንን ሁሉ እያወኩና እየተረዳሁ ይበልጥ መግፋት ወደፊት መሔድ እንዳለብኝ ተረዳሁኝ።
የእነዚሀ ኢትዮጵያውያን ክርስቲያን ወገኖች መራብ የኔም መራብ፣የነሱ መጠማት የኔም መጠማት ነው፣የነሱም መንገላታት ለእኔም መንገላታት ነው፣የነሱ ስቃይ የኔም ስቃይ ነው በማለት አቅሜ የቻለውን በሙሉ የድርሻዬን እየተወጣሁ እገኛለሁ።
እኛ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አማኞች፣
ትውልደ ኢትዮጵያውያን የሆንን ሁላችን፦
_ድንቅ ባህልና እሴቶች ያሉን
_ቀደምት አባቶቻችን የሰሩልን ትውፊት እና
  እሴት እንዳይጠፋና እንዳይሸረሸር
  ያስተማሩን፣ያሳወቁን
_የቅዱሳን ክብረ በዓል በሚከበርበት  
  ጊዜ እና ወቅት በቤተ ክርስቲያን 
  ምእመናን
  በአንድነት ሆነው ካላቸው ነገር ላይ
  በማዋጣትና በማስተባበር ዝክር
  በመዘከር
  በዓል በዓልነቱ እንዲመስል እና የቤተ
  ክርስቲያን ድምቀቷና ውበቷ የሆነውን  
  ዝክር ያስተማሩን
_ በዚህ በዝክር ውስጥ በዓሉ 
   ከሚከበርበት ከዋዜማው አንስቶ እስከ
   በዓሉ ፍፃሜ ድረስ አበው 
   ካህናት፣ምዕመናን፣አላፊው አግዳሚው
   የሚስተናገድበት፣
   ከሩቅም ከቅርብም ያሉ ነድያን/ 
   ተስፈኞች/ የሚመገቡበትና የሚረዱበት
   መንገድ ያሳወቁን
_ቤተ ክርስቲያን ድሀ ነው ሀብታም ነው
  ሳትል፣ገንዘብ አለው/የለውም/
  ታማሚ ነው/አይደለም/
  ብሔሩ ምንድነው ሳትል ሁሉንም 
  በአንድነት እንዲሳተፍ አድርጋ ያስተማረች 
  ሀይማኖታዊ ስርዓትን፣ትውፊትን
  ያሳወቀችን
_ድሆች፣አቅመ ደካሞች፣ፀበልተኞች
  አይምሮ ህሙማንን ወዘተ እንድናስባቸው
  ያደረጉን
_ሁላችን በጋራ
  በመተባበር፣በመተጋገዝ፣በመተሳሰብ፣
  እና ከተረፈን ሳይሆን ካለን ላይ
  ተካፍለን በጋራ እንደ ሀገር እንደ  
  ሀይማኖት እንድንቆም ያረጉን ናቸው።

እነዚህ ከላይ የጠቀስኳቸው በጎ ተግባራት እኛ ሰዎች / ትውልደ ኢትዮጵያውያን የሆንን ፤የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ልጆች አማኝ የሆንን በሙሉ መጠበቅ ማስጠበቅ ያለምንም መሰልቸት በትጋት፣በመፅናት በጋራ ይህንን ኢትዮጵያውነት/ክርስቲያናዊ ህብረት/አንድነት/ እያንዳንዱ ክርስቲያን ነኝ፣አማኝ ነኝ የሚል ሁሉ ባለበት ቦታ ሀይማኖታዊ ግዴታውን መወጣት ይገባዋል እላለሁ።

የዚህ አይነት በጎ ተግባር ውስጥ ያለን ደስታን፣ሰላምን፣ትዕግስትን፣ቸርነትን፣በጎነትን፣እምነትን፣የውሀነትን፣ቅንነትን፣ራስን መግሳትን፣መልካምነትን፣መተጋገዝን ከፈጣሪ የሚሰጥ/የሚቸር/የፀጋ ስጦታ መሆኑን መገንዘብ ይኖርብናል።

እኔም ወንድማችሁ
በእናንተ ቅን እና ደጋግ ልቦች እገዛ
የተሰሩ በጎ ተግባራት የተሰሩ መሆናቸውና ወደፊትም እነዚህ በጎ ተግባራት በተሻለ ከእንተ በማገኘው
ድጋፍ  ከቅዱስ ሚካኤል አማላጅነትና ተራዳኚነት ጋር ሙሉ ተስፋ አለኝ ብዬ አስባለሁ።
እንደሁል ጊዜውም ይህንን እቅድ ለማሳካት ዘወትር በፀሎት ለምታግዙኝና ለምትተጉ በሙሉ አዛውንት እናቶች አባቶች እንዲሁም ወንድሞችና እህቶች በሙሉ አሁንም በድጋሚ ቅዱስ ሚካኤል ይጠብቃችሁ፣ዋስ ጠበቃ ይሁናችሁ፣ለእርሱ እንደቆማችሁ እርሱ ይቁምላችሁ፣በሰላም ወታችሁ በሰላም ግቡ፣ልጆቻችሁ ይደጉ፣በማናቸው ነገሮች ሁሉ እርሱ ይድረስላችሁ እላለሁ።

Loading comments...