በእንተ ቅድሳት

6 months ago
78

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።፫
በእንተ ቅድሳት
👉አንድ ስለምታደርግ ስጋውና ደሙ     
     አግዚአብሔር በይቅርታው አንድ
     ያደርገን ዘንድ ሰላምን እንማልዳለን
👉እግዚአብሔር የሱን ሀይማኖት በንፁህ  
     እንድንጠብቅ ይሰጠን ዘንድ ስለ
     ሀይማኖታችን እንማልዳለን
👉እስከ ፍፃሜያችን ድረስ እግዚአብሔር
     በመንፈስ ቅዱስ አንድነት ይጠብቀን
     ዘንድ ስለ አንድነታችን እንማልዳለን
👉 በመከራችን ሁሉ እግዚአብሔር
      የትግስትን ፍፃሜ ይሠጠን ዘንድ ስለ
      ነፍሳችን ትዕግስት እንማልዳለን
👉ቅዱሳን ስሚሆኑ ነቢያት ከሳቸው ጋር
     እግዚአብሔር ይቆጥረን ዘንድ
     እንማልዳለን
👉እነሱ ደስ እንዳሰኙት ደስ ልናሰኘው        
     እግዚአብሔር ማገልገሉን ይሰጠን    
     ዘንድ ዕድል ፈንታቸውንም ያድል ዘንድ
     አገልጋዮች ስለሚሆኑ ሐዋርያት    
     እንማልዳለን
👉እግዚአብሔር ለኛ የሰማዕትነትን ስራ 
     ይሰጠን ዘንድ ቅዱሳን ስለሚሆኑ      
     ሰማዕታት እንማልዳለን
👉የቤተክርስቲያን አገልጋዮች እነሱ
     ናቸውና እግዚአብሔር እነሱን ለረጂም
     ወራት ይሰጠን ዘንድ ያለ ነውር
     በንፅህና ሁነው በዕውቀት የሀይማኖትን
     ቃል ያቀኑ ዘንድ ስለ ርእሰ ሊቃነ
     ጳጳሣችን ስለ አባ ማትያስ ብፁዕ
     ስለሚሆኑ ሊቀ ጳጳሣችንም አባ ሔኖክ   
     እንማልዳለን
👉የክህነትን ስልጣን ከእነሱ
     እግዚአብሔር እንዳያርቅ  
     መትጋትን እሱን መፍራትንም
     እስከ ፍፃሜ ይሰጥልን ዘንድ
     ድካማቸውንም ይቀበል ዘንድ
     ስለ ቀሳውስት እንማልዳለን።
👉ፈፅመው ሊፋጠኑ መፋጠንን
     እግዚአብሔር ይሰጣቸው ዘንድ
     በቅድስናም ይቀርቡ ዘንድ
     ድካማቸውንና ፍቅራቸውንም ያስብ
     ዘንድ ስለ ዲያቆናት እንማልዳለን
👉የሀይማኖታቸውን ትጋት ሊፈፅሙ   
     እግዚአብሔር ይሰጣቸው ዘንድ ስለ
     ንፍቀ ዲያቆናት ስለ አንባቢዎችም
     ስለመዘምራንም እንማልዳለን
👉ልመናቸውንም ይሰማቸው       
     ይልቁንም የመንፈስ ቅዱስን ሀብት   
     በልቦናቸው ያሳድርባቸው ዘንድ   
     ድካማቸውንም ይቀበል ዘንድስለ   
     ባልቴቶች ረዳትም ስለሌላቸው     
     እንማልዳለን
👉እግዚአብሔር የድንግልናቸውን
     ዋጋ(አክሊል) ይሰጣቸው ዘንድ
     ለእግዚአብሔርም ወንዶችም ሴቶችም
     ልጆች ይሆኑት ዘንድ ስለ ደናግል
     እንማልዳለን
👉በመታገሳቸው ዋጋቸውን ይቀበሉ ዘንድ
     እግዚአብሔር እንዲሠጣቸው      
     ስለሚታገሡ ሰዎች እንማልዳለን
👉በንፅህና ሁነው ይጠበቁ ዘንድ
     እግዚአብሔር ፍፁም ሀይማኖትን   
     እንዲሠጣቸው ስለ ሕዝባውያንና ስለ   
     መሀይምናን እንማልዳለን
👉በጎውን ዕድል ኃጢአትን ለማስተሥረይ
     ሁለተኛ መወለድ የሚገኝበትን ሕፅበት
     እግዚአብሔር ይሰጣቸው ዘንድ
     በቅድስት ስላሴ ማህተም ያከብራቸው
     ያትማቸው ዘንድ ስለ ንዑሰ ክርስቲያን
     እንማልዳለን
👉በዘመኑ ሁሉ ፍፁም ሰላምን
     እግዚአብሔር ይሰጣት ዘንድ ስለ
     ኢትዮጵያ እንማልዳለን
👉ዕውቀትን እሱን መፍራትንም   
     እግዚአብሔር ይሰጣቸው ዘንድ
     ስለመኳንንትና ሥልጣን ስላላቸው
     እንማልዳለን
👉ስለ ዓለሙ ሁሉ እግዚአብሔር ማሰብን
     ያስቀድም ዘንድ እያንዳንዱም
     የሚያስፈልገውን ያማረውን
     የሚሻለውንም ያስብ ዘንድ ስለ ዓለሙ
     ሁሉ እንማልዳለን
👉እግዚአብሔር ይቅርታ ባለው ቀኝ
     መርቶ በፍቅር እና በደኅንነት ወደ
     ማደሪያቸው ይመልሳቸው ዘንድ     
     በባህር እና በየብስ ስለሚሄዱ ሰዎች   
     እንማልዳለን
👉እግዚአብሔር የዕለት የዕለት
     ምግባቸውን ይሰጣቸው ዘንድ
     ስለተራቡና ስለተጠሙ ሰዎች
     እንማልዳለን
👉እግዚአብሔር ፈፅሞ ያረጋጋቸው
     ዘንድ ስለአዘኑና ስለተከዙ
     ሰዎች እብማልዳለን
👉 እግዚአብሔር ከእስራታቸው
      ይፈታቸው ዘንድ ስለ ታሰሩ ሰዎች
      እንማልዳለን
👉ግዚአብሔር በሰላም ወደ አገራቸው
     ይመልሳቸው ዘንድ ስለተማረኩ ሰዎች
     እንማልዳለን
👉እግዚአብሔር ትዕግስትን በጎ
     ትምህርትንም ይሰጣቸው ዘንድ
     የድካማቸውንም ፍፁም ዋጋ
     ይሰጣቸው ዘንድ ስለ ተሰደዱ ሰዎች   
     እንማልዳለን
👉እግዚአብሔር ፈጥኖ ያድናቸው ዘንድ
     ይቅርታውንና ቸርነቱንም
     ይልክላቸው ዘንድ ስለታመሙና ስለ
     ድውያኑ እንማልዳለን
👉ከቅድስት ቤተክርስቲያን ወገን ስለ
     ሞቱ ሰዎች እግዚአብሔር
     የዕረፍት ቦታ ይሰጣቸው ዘንድ
     እንማልዳለን
👉እግዚአብሔር እንዳይቀየማቸው
     ከመዓትም ተመልሶ ፍጹም
     ዕረፍትን ይሰጣቸው ዘንድ ስለ በደሉ
     አባቶቻችን እና ወንድሞቻችን
     እንማልዳለን፤
👉በሚያስፈልግበት ቦታ እግዚአብሔር
     ዝናሙን ያዘንብ ዘንድ ስለ
     ዝናብ እንማልዳለን
👉የወንዙን ውሃ ምላልን ብለን
     እግዚአብሔር እነሱን እስከ
     ልካቸውና እስከ ወሰናቸው ይመላ
     ዘንድ ስለወንዝ ወሃ እንማልዳለን
👉ለዘር እና ለመከር ሊሆን እግዚአብሔር
    ለምድር ፍሬዋን ይሰጣት ዘንድ ስለ
    ምድር ፍሬ እንማልዳለን
👉በጸሎት የምንለምንና የምንማልድ
     ሁላችንንም:-
በሰላም በመንፈስ ይጠብቀን
ፍቅርንም ይስጠን
ዓይነ ልቡናችንንም ያብራልን
ፈቃዱም ሆኖ ጸሎታችንን ይቀበል ዘንድ ቀርበን እግዚአብሔርን እንለምነው
ዐውቀን በሃብቱ እናድግ ዘንድ
በእርሱም ስም እንመካ ዘንድ
በነቢያት በሐዋርያትም መሰረት ላይ እንታነጽ ዘንድ
እንግዲህ በመንፈስ ቅዱስ እንነሳ ቀርበን አምላካችን እግዚአብሔርን እንለምነው ወዶ ጸሎታችንን ይቀበል ዘንድ።

Loading comments...