አርበኛ ዘመነ ካሴ እና ሌሎች አመራሮች ምን አሉ/ታላቁ ኦርኬስትራ ባንድ ምስረታ እና አብዮቱ/1ኛ አመት የአማራ አብዮት በዓል በድምቀት ተከበረ

9 months ago
485

የአማራ ፋኖ በጎጃም ፩ኛ ዓመት "የአማራ አብዮት" በዓልን አርበኛ ዘመነ ካሴን ጨምሮ የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት አከበረ።

በመላው አማራ ክልል የኢንተርሃሞይ ባህርይ የተላበሰው የብልጽግና ሠራዊት በመላው አማራ ክልል በብልጽግና ፓርላማ በሕግ የተደገፈ ወረራ መፈጸም ከጀመረ እነሆ ፩ ዓመት ሞላው።

የክልሉን የጸጥታ መዋቅር በሦስት ቀናት ብቻ ብትንትኑን ያወጣው የአማራ ፋኖ ወራሪውን ሠራዊት በመመከትና በማጥቃት የአማራን ሕዝብ አንገት ቀና በማድረግ ላለፉት ፩ ዓመት ከባድ ተጋድሎ አድርጓል።
በዚህ ፩ ዓመት ውስጥ በፈጀው ጦርነት እናቶች፣ አዛውንቶች እና ሕጻናት ሕዝብ በከፈለው ግብር በሚገዛ የድሮን አረር ተጨፍጭፈዋል።በርካታ ጀግና ፋኖዎች የጠላትን ጉረሮ በመተናነቅ ክቡር መስዋዕትነት ከፍለዋል። የፋኖ ኃይል ግዙፍ ወታደራዊና ፖለቲካዊ ቁመና ከመላበሱ ባሻገር በምሥራቅ አፍሪካ ወሳኝ ተዋናይ ሆኗል፤ዓለም አቀፍ ትኩረትንም ስቧል።
ከብዙ አስርት ዓመታት በኋላ የአማራ ትግል በአዲስ ፖለቲካዊ እይታ እና በብሩህ ተስፋ እንዲመራ ያደረገው አዲሱ የአማራ ትውልድ በራሱ እጅ የጻፈውን ታሪክ በራሱ ልጆች መዘከር እንዳለበት ይታመናል።
በመሆኑም ይህንና መሰል ድሎችን ማክበር እና ሰራዊቱን ለበለጠ ተጋድሎ ማነሳሳት ሰማእታትንም ማክበር ይቻል ዘንድ የአማራ ፋኖ በጎጃም ሳምንቱን የትግሉ ችቦ የተለኮሰበትን በዓል እንዲታሰብ በወሰነው መሰረት በዛሬው እለት የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ተከብሯል።
በዚሁ ክብረ በዓል ላይ የእኛ ትውልድ ኦልኬስትራ ባንድም በይፋ ተመስርቶ ስራውን ጀምሯል።

Loading comments...