ኮሎኔሉ ፋኖን ተቀላቀለ | ፋኖን የተቀላቀለው ኮሎኔል ለ251 | "አሳማ ከመሆን አንበሳ መሆንን መርጬ ፋኖን ተቀላቅያለሁ" | Ethio 251 Media |

3 months ago
556

ከኢትዮ 251 ሚዲያ የቀረበ ጥሪ!

ኢትዮ 251 ሚዲያ ላለፉት አራት ዓመታት የዐቢይ አህመድ አገዛዝ በአማራ ህዝብ ላይ የሚያደርሰውን መጠነ ሰፊ ጭፍጨፋና ግፍ እየተከታተለ በመዘገብ የህዝብ ልሳን ሆኖ መቆየቱ ይታወቃል፡፡

ሆኖም ሚዲያው በሚያቀርባቸው መረጃዎች አገዛዙን በማጋለጡ፤ አገዛዙ ሚዲያውን በመዝረፍ፣ ጋዜጠኞችን በማሳደድ እንዲሁም በተደጋጋሚ እና በተደራጀ መልኩ ቻናሎቹን እያዘጋበት ይገኛል፡፡

በዚህ የተነሳም የአማራ ህዝብ የተጋረጠበትን የዘር ማጥፋት ጦርነት ሰሚ እንዳያገኝ የአገዛዙ ፍላጎትና እቅድ ቢሆንም፤ ኢትዮ 251 ሚዲያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሆኖም ለህዝብ ድምጽ በመሆን የአገዛዙን ገመና ያለማቋረጥ እያጋለጠ ይገኛል፡፡

በመሆኑም የአማራ ህዝብ የተጋረጠበትን ጦርነት ለመመከትና ህልውናውን ለማስጠበቅ የሚዲያው ሚና ከፍተኛ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ኢትዮ 251 ሚዲያም ይህንን ኃላፊነቱን በመረዳት ባለሙያዎች በመጠናከርና በሁሉም ቀጠናዎች ዘጋቢዎችን በመመደብ እየሠራ ይገኛል፡፡ ይህ ጥረቱም የአገዛዙን ገመና ከማጋለጥም በተጨማሪ፤ የፋኖን እያንዳንዱን የትግል ውሎና ጀብዱ በመዘገብና ሰንዶ በመያዝ ላይ ነው፡፡

ይህን ጥረቱን በተጠናከረ መልኩ እንዲያከናውን የፋይናንስ ድጋፍ አስፈላጊ ሆኖ አግኝቶታል፡፡

ስለሆነም ኢትዮ 251 ሚዲያን በዚህ የጎፈንድሚ አካውንት በመደገፍ የአማራን ህዝብ ትግል ይደግፉ ስንል በአክብሮት ጥሪ እናቀርብለዎታለን፡፡

ኢትዮ 251 ሚዲያ!!

https://gofund.me/a2d99937

Loading 1 comment...