የቅዱስ ሚካኤል መዝሙር - Ye Kidus Mikael Mezmur

4 months ago
107

ውድ የድንግል ማሪያም ልጆች ሰብስክራይብ እያደረጋችሁ ቤተሰብ ሁኑን...
https://www.youtube.com/channel/UCF-7iihetxm3QQ_EVh0vjUw?sub_confirmation=1 🙏🙏❤❤🙏🙏

የአፎሚያ ረዳት ነህ ሚካኤል /2/
ቅሩበ እግዚአብሔር የልዑል
ፈጥነህ ድረስልን ስንጠራህ ሚካኤል
ፊት ለፊታችን አምላክ ሰደደህ
አቀናህልን መንገዱን ጠርገህ
የቤልሆርን ምክር አፈረስክ
ከልጆችህ ጋር ከነዓን ደረስክ
ከኛ ጋር ነበርክ አርባውን ዘመን
እንጠራሃለን ሚካኤል ብለን
በቃዴስ ክንፍህ ተዘርግቶልን
ደመናው ባንተ ተጋረደልን
አብረህን ልትሆን ጌታ የላከህ
አንተ ሚካኤል ታዳጊያችን ነህ
ሙሴ ሲለየን ደጉ አባታችን
ሚካኤል ነበርክ ከላይ መሪያችን
የባርነቱ ጉዞ እስኪያበቃ
እጅግ ረዳን የኛ ጠበቃ
ሳጥናኤል መክሮን የሀሰት ምክር
ሊወስደን ሻተ ሙሴ መቃብር
ስለማይጠቅመን አንተ ሰወርከው
ምክሩን በታትነህ አስጎነበስከው

Loading 1 comment...