ቋሚ መንግስት ወይንስ የሽግግር መንግስት ፡ ዶር ደብሩ ነጋሽ

1 year ago
74

የኃይሌ ፊዳን የሕይወት ታሪክ ፀሐፊው ዶር አማረ ተግባሩ፡ የአብይ አህመድ ከሥልጣን መወገድና የሽግግር መንግሥት አስፈላጊነት በሚል አርእስት አንድ መጣጥፍ ሰንደው ዘ ሃበሻ ድህረ ግፅ ላይ አስነብበዋል https://amharic-zehabesha.com/archives/183768፡ ከታሪክ እንደምንረዳው በ1966 የኢትዮጵያ ሕዝብ አመፅ በወታደሩ ተነጥቆ ከተወሰደ በኋላ ከደርግ መንጋጋ ስልጣን ለመቀማት ከአውሮፓ ፈርጥጦ ወደ አገር ቤት የገባው ድርጅት መኢሶን ነበር ፡ ዶር አማረም የመኢሶን አባል የነበሩ እንደነበሩ ከመአዛ ጋር ያደረጉት ቃለ መጠይቅ ላይ ተጠቅሷል ፡፡https://www.youtube.com/watch?v=cQNlgwOGjlM&ab_channel=ShegerFM102.1Radio ፡፡ የመኢሶን እጣ ፋንታ ምን እንደሆነ ሁላችንም የምናውቀው ጉዳይ ነው ፡፡ ሙሁሩ ከራሳቸው ከታሪክ ተምረው የመንግስት ለውጥ እንዴት ይመጣል የሚለውን ያጡታል የሚል እምነት የለኝም ፡ ነገር ግን የኢትዮጵያ ሕዝብ ከፍተኛ ሰቆቃ ላይ በወደቀበት እና ስር ነቀል ለውጥ በሚያስፋልግበት ሰአት አብይ የሽግግር መንግስት አደላድሎ ስልጣኑንን እንዲያስረክብ ጥሪ አቅረበዋል ፡፡ ምንም እንኳን እሳቸው ለውይይት ብለው ቢያቀርቡትም የሽግግር መንግስቱ ጥሪ ነባራዊ እውነታን ያላገናዘበ ፡ የአብይን መንግስት ለማቆየት የታቀደ ፡ ሙሁራዊ ቀልድ ቀልደዋል፡፡ ይህን በተመለከተ ዶር ደብሩ ነጋሽ ከዕውነት ሚዲያ ጋር ቆይታ አድርጓል ፡ አዳምጡት ፡ አጋሩት ፡ ተወያዩበት ፡፡ ስር ነቀል ለውጥ ወይስ የሽግግር መንግስት ፡፡

Loading comments...