በዶር ደብሩ ነጋሽ ለዶር ዮናስ ብሩ የተሰጠ መልስ፡ "ፅንፈኛ ብሔርተኝነት እንጂ ፅንፈኛ ኢትዮጵያዊነት የለም"

10 months ago
106

ዶር ዮናስ ብሩ የአብይን መንግስት ለማገልገል ሻንጣቸውን ከምደረ አሜሪካ ሽክፈው ወደ አገር ቤት ከገቡ ሙሁራን አንዱ ናቸው፡፡ የምጣኔ ሃብት ባለ ሞያ የሆኑት ዶር ዮናስ ብሩ የአብይ አስተዳዳር በፈለጉት መልኩ ስላላስተናገዳቸው ከአሜሪካ የሸከፉትን ሻንጣ ተሽክመው ወደ አሜሪካ ተመልሰዋል፡፡ ነገር ግን ዶር ዮናስ አሜሪካም ሆነው የአብይን ክፍ ማየት አይፈልጉም ፡፡ በልባቸው ያነገሱትን አብይ አሁንም ቢሆን ከነ ብልሽቱ ቢቀጥል ይመኛሉ፡፡ በእሳቸው እይታ የአብይን የግፍ አገዛዝ የሚቃወም ሁሉ ፅንፈኛ ነው ፡ ፅንፈኛ አማራ፤ ፅንፈኛ ፋኖ፡ ፅንፈኛ ኢትዮጵያዊ፡፡ ለእሳቸው ፅንፈኛ ያለሆነው እና ቅዱሱ ፡፡ ኦሮሙማ ፡ ኦነግ ሸኔ ፡ አብይ ፡ ጁዋር፡ ኦቦ ሽመልስ ወዘተ ናቸው ፡፡ ይህን ሃሳባቸውን ለማጠናከር እና የሕልውና ትግሉን ለማኮሰስ ብሎም ለማኮላሸት፡ የሕልውናውን ትግል ለማጠልሸት ዶክተሩ ውስጠ ወይራ የሆነ አንድ ፅሁፍ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዋች አበርከተዋል ፡ ማንበብ ለምትፈለጉ ማስፈንጠሪያው እነሆ https://eastafricanist.com/averting-civil-war-in-ethiopia/ የፅሁፋቸውም አርእስት AVERTING CIVIL WAR IN ETHIOPIA ፡AN EMERGENCY MANIFESTO የሚለ ነው ፡አዛኝ ቅቤ አንጓች አሉ

ይህን በተመለከተ ዕውነት ሚዲያ ከዶር ደብሩ ነጋሽ ጋር ቆይታ አድርጋለች፡፡ ዶር ደብሩ ነጋሽም የሚከተለውን መልስ አጋርቶናል እና በጥሞና ያዳምጡት ፡ሰምተው ያገሩት አስተያየት ይስጡበት

የአንድ ሙሁር ሙሁራዊ ተግባር እና መለኪያወ የሰማውን ሰምቶ ዝም ማለት ወይም ያወቀውን አውቆ የጋን መብራት መሆን ሳይሆን ያላወቀን ያለሰማውን ሕዝብ ማሰማት እና ማሳውቅ ነው፡፡ በእዚህ ተግባር ዶር ደብሩ ከፍተኛ አተዋፅዎ እያደረገ ነው ፡፡ ትርክት ማፈርስ ፡ የትግሉ አንዱ አካል ነው፡፡ የኦሮሞ ( ጋላ) ሊሂቃን ያልተፃፋ ፡ተፃፋ ያለነበር ነበረ፡ ያለተደረገ ተደረገ ሲሉ ሌላው ሙሁር ዝም ብሎ መቀመጥ አና መስማት የለበትም ፡፡ ዕውነት ሚዲያ ፡፡

በዕውነት ሚዲያ ቀርባችሁ መወያተ ለምትፈልጉ ሚዲያው ክፍት መሆኑን በትህተና እናሳውቃለን፡፡ ፃፉልን

Loading comments...