ፋኖ ለነጻነት ✊🏿

1 year ago
37

#ኢትዮጵያ'ዊነት ውድ መልኬ ነጋ ጠባ አትነካኩት፤
አላወልቅም ባንዲራዬን ልቤ ላይ ነው የለበሰኩት።

ከልቤ ላይ አላጠፋም የ'#ሐበሻ'ነት ታሪክ ውርሴን፤
እሰዋለሁ ለአንዲት ሀገር አንዲት ነፍሴን።

#ፋኖ ለነጻነት ✊🏿
#ፋኖ ለአንድነት ✊🏿
ይዘምታል ምንጊዜም ለ'#ኢትዮጵያ'ዊነት /፪/ ✊🏿

ሜዳ ገደል ፀሐይ ብርዱ አልፈዋለሁ ሁሉን ችዬ፤
ለህጻናት ለአዛውንቱ ለሰው ክብር ብቻ ብዬ፤
ለነጻነት ብዬ።

የአባቶቼን ፈለግ ስለምደጋግም፤
የበላይን ታሪክ በታች አላረግም!

የፋኖነት ገድል የፋኖነት ክብሬ፤
ብሞትም ለአንድ ሀገር ብኖርም ለሀገሬ።

አቤት ብዬ ተጠርቼ ተሰልፌ በፋኖ ሰም፤
የተሰዉት ጓደኞቼ 'የደም ዋጋ አላርክሰም።' /፪/

#ፋኖ ለነጻነት፤
#ፋኖ ለአንድነት፤
ይዘምታል ምንጊዜም ለ'#ኢትዮጵያ'ዊነት። /፪/

𖧞𖧞𖧞
💚💛❤️
🙏🏿🙏🏿🙏🏿

Loading comments...