በሁለት የስሜት ፅንፍ ውስጥ መዋለል ባይፖላር ዲስኦርደር | ባይፖላር ዲስኦርደር ምንድነው? በምን ይከሰታል? መፍትሔውስ?

1 year ago
29

እንኳን ወደ የአለማችን tube በሰላም መጡ !! ይህን ቻናል ሰብስክራይብ በማድረግ የአለማችን ድንቃድንቅ ሰዎች ክስተቶች ግኝቶች እና እውነታዎችን ይከታተሉ የአለማችን ቲዩብ በአለም ዙሪያ ያሉ አስደናቂ እውነታዎችን ወደ እናንተ የሚያደርስ ቲዩብ ነው ፡፡ አለምን ጉድ ያስባሉ እውተታዎችን ወደእናንተ እናደርሳለን፡፡
Welcome to አለማችን Tube.Please subscribe and Be part of the world's YouTube family and follow the discoveries and facts of the world's amazing people Biography,biography: the life of,famous biographies,biography facts,famous people biography,biographies of famous people,famous,personalities,famous persons,እውነተኛ ታሪክ,አስገራሚ ታሪክ,አስደናቂ ታሪክ,አስገራሚ እውነታዎች,Lexurylife,ቢሊየነርሚሊየነር,Wealth,Dollars,ሀብታም,ሀብት,Lucy Tip,Fana Television,Nahoo TV,Kana drama,Kana Television,EBS TV WorldWide,JTV Ethiopia,New Ethiopian music,New Ethiopian Movie,Hope Music Ethiopia,seifu on ebs,seifu fantahun This channel is the place to find different mysteries about nature, humans, animals and worldwide events. With daily videos packed with funny, scary, crazy and sometimes sad information’s that you have never heard of.
#የአለማችንTube
#ethiopian
#Ethiopia
#science
#technology
#health
ባይፖላር ዲስኦርደር ምንድን ነው?
ባይፖላር ዲስኦርደር የስሜት መዋዠቅ ነው።
ሕመሙ ሁለት ጽንፎች አሉት። አንደኛው ጽንፍ የድብታ ሲሆን፣ ሌላኛው ደግሞ የተትረፈረፈ ደስታ፣ የስሜት ትፍስህት የሚጎርፍበት ነው።
በዚህ በሽታ የተያዘ ማንኛውም ሰው በሁለቱ ጽንፎች መካከል ይዋልላል። ድብታው ሲጫነው ከዚያ ለመውጣት መድኃኒት ይሰጠዋል።
ይህ መድኃኒት ደግሞ ከእውነታው ዓለም ወደ ተፋታ ስሜት እንዳያስገባው ሌላ መድኃኒት ጨምሮ መውሰድ ይኖርበታል።
እሌኒም ለዚያ ነው የተለያዩ መድኃኒቶች ቅንብር እንደምትወስድ የምትናገረው።
በድባቴ ውስጥ የሚሆን ሰው ነገሮችን በአሉታዊ ጎኑ ብቻ መመልከት፣ መንቀሳቀስ እና መስራት አለመቻል፣ አቅም እና እንቅልፍ ማጣት፣ የምግብ ፍላጎት አለመኖር፣ አቅም ኖሮት ቢሆን እንኳ መንቀሳቀስ አለመቻል መገለጫዎቹ ናቸው።
ሌላኛው ጽንፍ ደግሞ ‘ማኒክ’ (manic) የሚባለው ነው።
በዚህ የስሜት ጽንፍ የሚንገላታ ግለሰብ በጣም ኃይለኛ ጉልበት ይኖረዋል። እንቅልፍ አይተኛም።
ራስን በጣም ከፍ አድርጎ መመልከት ይኖራል።
እሌኒ ይህ ስሜት ውስጥ ስትሆን የሚሰማትን ስታስረዳ “ራሴን ከፈጣሪ አንድ ልዩ ተልዕኮ አንደተሰጠው ሰው አድርጌ እቆጥራለሁ። በጣም የተትረፈረፈ ከፍተኛ ደስታ ይሰማኛል። ከሰው ጋር ለመነጋገር፣ ለመወያየት አቅም ይኖረኛል” ትላለች።
ሌላ ጊዜ ለመስራት የማትደፍረውን በዚያ ወቅት ለመስራት እንደምትደፍር፣ ገንዘብ በጣም እንደምታባክንም ትናገራለች።
“ሁሌ ለሁሉ ሰው መስጠት ነው. . . አንድ ጊዜ የተትረፈረፈ ደስታ፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ የድብታ ሸለቆ ውስጥ የመግባት ስሜት ይሰማኛል።”
በዚሁ በሁለት የስሜት ደርዞች ውስጥ ለሚዋልል ሰው የሚሰጡት የመድኃኒት ቅንብር የሚረዱት ያሉበትን ስሜት ለማስተካከል ነው።
“ሁሉንም ዓይነት ስሜቶች አስተናግጃለሁ፤ እኔ ጋር ብዙ ጊዜ የሚታየው ድብታው ነው” የምትለው እሌኒ ድብታ ውስጥ ስትሆን ሥራ መስራት አለመቻል፣ ትኩረት ማጣት ይፈትኗት እንደነበር ትናገራለች።
ካለችበት የስሜት ጽንፍ ለመውጣት ከሚሰጣት መድኃኒት ባሻገር የሕክምና ባለሙያዎች ምክር እንድትረጋጋ እንደሚረዳት ገልጻለች።
ምክንያቱ ምን ሊሆን ይችላል?
ባይፖላር ዲስኦርደር በምን ምክንያት እንደሚከሰት እስካሁን ድረስ ይህ ነው የሚባል የተረጋገጠ ምክንያት የለም።
ነገር ግን ከቤተሰብ መካከል በዚህ ሕመም ያጋጠመው ሰው ካለ፣ ሌሎች የቤተሰብ አባላት ላይ የማጋጠም ዕድሉ ከፍተኛ መሆኑን የሕክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ።
ለበርካታ ሰዎች ችግሩ የሚቀሰቀሰው በእድሜ ከፍ ካሉ በኋላ ቢሆንም፣ እንደ እሌኒም በአፍላ እድሜያቸው ላይ ያሉ ሰዎች ላይም ሊከሰት ይችላል።
በአፍላዎቹ እድሜ በዚህ የስሜት መዋዠቅ የአእምሮ ጤና ችግር ለሚያጋጥማቸው ሰዎች ምክንያት ሊሆን ከሚችሉ ነገሮች መካከል፤ የሕይወት መስመር በድንገት መቀየር፣ በተለያየ ምክንያት ከቤተሰብ ርቆ መሄድ እንዲሁም የሚወዱትን ሰው ማጣት ሊሆኑ ይችላሉ።
‘ምልክቶቹን ለምጃቸዋለሁ’
እሌኒ እንደምታስረዳው ባይፖላር ዲስኦርደር ያለበት ሰው ላይ የሚታዩት የሁለቱም ጽንፎች ምልክቶች አሉት።
ከሕመሙ ጋር ረዥም ጊዜ በመቆየቷ ምልክቶቹን ቀድሞ የማወቅ ልምድ አዳብራለች።
"ወደ ድባቴ ውስጥ የምገባ ሲመስለኝ በጣም እንቅልፍ እተኛለሁ። ቶሎ ቶሎ ስሜቴ ይለዋወጣል። ሌላ ጊዜ ማድረግ የሚያስደስተኝን ነገር ስሜት አጣበታለሁ። እንደዚህ ዓይነት ስሜቶች ሲኖሩ ወደ ድባቴ እየገባሁ እንደሆነ እገምታለሁ።”
እርሷ ብቻ ሳትሆን ቤተሰቦቿም እነዚያን ምልክቶች ካዩ መድኃኒት መውሰዷን ይጠይቃሉ።
“ትንሽ ስሜት ለውጥ ራሴ ላይ ስመለከት ቶሎ ወደ ህክምና ተቋም በመሄድ መድኃኒቶቹ እንዲስተካከል ይረዱኛል። የምክር አገልግሎት ይሰጠኛል” ትላለች።
“ሌላኛው ጽንፍ ደግሞ እንቅልፍ ሳልተኛ ስቀር፣ አእምሮዬ በጣም ከሚገባው በላይ ንቁ ሲሆን፣ ሌላ ጊዜ የማልደፍረውን ሰው በድፍረት መናገር ስጀምር፣ ገንዘብ አያያዝ ላይ ከዚህ በፊት የማላደርገውን ዝም ብዬ ሳደርግ፣ ቶሎ ወደ ሃኪም ቤት እሄዳለሁ።”
ባይፖላር ህመም ከምንም በላይ ራስን መግራት፣ ራስን በሥርዓት መምራት ይጠይቃል ትላለች እሌኒ።
“ምክንያቱም የተረጋጋ ሕይወት ለመምራት የሕይወት ዘይቤን ማስተካከል ይጠይቃል። ብዙ ደስታዎች ያሉበት ቦታ ወይንም ደግሞ ይህንን ስሜት የሚቀሰቅሱ ቦታዎች ላይ መቆየት የለብኝም።”
“ወደ ተትረፈረፈ ደስታ እየሄድኩ ከሆነ መቀነስ ያለብኝ የማኅበረሰብ ግንኙነቶች ይኖራሉ። ራሴን ገታ ማድረግ ይኖርብኛል።”
የመድኃኒት ቅንብር
እሌኒ ከስድስት ወር በፊት ሥራ መስራት፣ ትኩረት ማድረግ እንዳቃታት ታስታውሳለች።
“ደስታ አጣሁ፣ እንቅልፍ ሌሊት አይወስደኝም። ተኝቼ ጠዋት ስነቃ በሚገባ አልነቃቃም። እንቅልፍ ብተኛም የተኛሁ ያህል እርፍ ብዬ አልነሳም። አልቅሽ አልቅሽ ይለኛል” ትላለች የነበረችበትን ሁኔታ ስታስታውስ።
ያኔ የገባችበትን ድብታ የሚቀንስ መድኃኒት ተሰጣት።
“ይህንን መድኃኒት ደግሞ በሚገባ ካልተቆጣጠርነው ወደ ማይፈለገው እና ወደ ተትረፈረፈ ደስታ መውሰድ አቅም አለው። ስለዚህ አብሮ ያንን ገታ የሚያደርግ መድኃኒት መውሰድ አለብኝ።”
ምንጊዜም ድብታ ውስጥ ስትገባ የሚሰጣት መድኃኒት፣ ከእውነታው ዓለም ወደ ሚቃረን ሁኔታ ውስጥ እንዳያስገባት ሌላ መድኃኒት አብራ እንድትወስድ ይደረጋል።
“በተጨማሪ ሙድ ስታቢላይዘር [ስሜትን የሚያረጋጉ] እወስዳለሁ” ትላለች።
እነዚህን መድኃኒቶች በአንድ ላይ መውሰድ ከባድ መሆኑን የምትናገረው እሌኒ፣ አንዳንዴ የትኛውን መድኃኒት መውሰድ እንዳለባ መለየት እና እርሱን መጠቀም እንደሚጠይቅ ታስረዳለች።
ከእርሷ ጋር የሚስማማ መድኃኒት እስኪገኝ ድረስ ሌላ መሞከርም እንደሚኖርም አልሸሸገችም።
“የጎንዮሽ ጉዳት ይኖረውና መቀየርም ይኖራል” ትላለች። በዚህ ጊዜ ሁሉ የስሜት መዋዠቅ እንደሚያጋጥም እና የተስተካከለ ነገር ላይ እስኪደረስ እንደሚያስቸግር ትገልጻለች።
“የተስማማኝ ሙድ ስታብላይዘር ከአገር ውስጥ ሲጠፋ ደግሞ ሌላ መድኃኒት መቀየር ይጠይቃል። ያኔ ደግሞ የስሜት መዋዠቅ ይከሰታል።"
አንድ መድኃኒት ከቅንብሩ መጉደል ወይንም መቀየር የስሜት መዋዠቅ፣ ከድብታ ወደ ተትረፈረፈ ደስታ ይጥላል።
የቤተሰብ ድጋፍ
እሌኒ የጤንነት ሁኔታዋ ባላወላዳ ጊዜ ሁሉ ቤተሰቦቿ ከጎኗ መሆናቸውን ትናገራለች።
በተለይ አግብቼ ለሦስት ዓመት ያህል ምንም ዓይነት ሕመም አልነበረኝም ስትል ትመሰክራለች።
ቤተሰቦቿ የስሜት መዋዠቅ ሲኖር ቀድመው ስለሚያውቁ፣ ሕክምና ድጋፍ እንድታገኝ ያስታውሷታል፣ መድኃኒቷን እየወሰደች መሆኑን ያረጋግጣሉ።
“ከነበረው ባሕሪ ውጪ የሆኑ ነገሮች ሲሆኑ የበለጠ የሚታወቀው ለውጪ ሰው ነው።”
በተለይ ሕሙማን ከእውነታው ዓለም የራቀ ስሜት ውስጥ በሚገቡበት ወቅት፣ አንዳንዴ ድምጽ መስማት፣ ለብቻ መነጋገር ይኖራል። ይህንን የሚለየው ቤተሰብ ነው።
ድብታ ከሆነ ግን በአብዛኛው ሕመምተኛ ግለሰቡ ራሱ ያውቀዋል።
ባይፖላር ችግር ያለበት ሰው ያለጭቅጭቅ፣ ሰላማዊ ኑሮ እንዲኖር ማድረግ ወሳኝ ነው።
በዚህም “እኔ በጣም ተጠቅሜያለሁ፤ ካገባሁ በኋላ ሦስት ዓመት ሙሉ ያለምንም ምልክት ነው የኖርኩት” በማለት የቤተሰብ ድጋፍ አስፈላጊነትን ትናገራለች።

Loading comments...