Honor for our Patriots - ክብር ለጀግኖቻችን - የ1969 ዓ.ም. የሶማልያ ጦርነት ጀግና የኮ/ል ባጫ ሁንዴ አካል በኢትዮጵያ በክብር ሊያርፍ ነው

Enjoyed this video? Join my Locals community for exclusive content at etafclub.locals.com!
1 year ago

የኢትዮጵያ አየር ኃይል አባላት ለሀገራቸው ሉዓላዊነትና የአየር ክልሏ ታፍሮና ተከብሮ መቀጠል በቁርጠኝት የከፈሉት የዘመናት መስዋዕትነት የሚዘከርበት ቀን አሁን ነው፡፡ ከእነዚህ ጀግኖች መሀከልም ኮሎኔል ባጫ ሁንዴ አንዱ ሲሆን፣ በአየር ኃይሉ ውስጥ በቴክኒሽያንነት ና በአብራሪነት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረከተ፣ በተለይ በኦጋዴን ጦርነት በኤፍ 5 ኢ አይሮፕላን አብራሪነቱ በአየር ላየር ውጊያ በጣላቸው አይሮፕላኖች ሳቢያ በሀገር ደረጃ ለላቀ የጦር ሜዳ ጀብዱ ሜዳይ ሽልማት ተሸላሚ የሆነ ጀግና ገድል የሚዘከርበት ልዩ እንቅስቃሴ እነሆ ጀምሯል፡፡ ይህ ቪዲዮም የዚያን ‹‹ለጀግኖች ክብርን የመስጠት›› ራዕይ ማሳያ ነው፡፡
የኢትዮጵያ አየር ኃይል በብዙዎች ኢትዮጵያውያን የዘመናት መስዋዕትነት የተገነባ፣ ከአብዛኛዎቹ የአፍሪካ ሀገሮች ቀደምት የሆነና ለሌሎችም አርዓያ በመሆን ያስመሰከረ ተቋም ሲሆን፤ በኦጋዴን ጦርነት የመሣሪያ ብልጫ ሳይበግራቸው እውቀትና ችሎታቸውን ብቻ በመጠቀም የጠላታቸውን አይሮፕላኖች በተደጋጋሚ በመጣል ሀገራቸውን ለድል ያበቁ አብራሪዎችንና ከፍተኛ የቴክኒክ ብቃትና ልምድ የተጎናፀፉ ቴክኒሽያኖችን ያፈራም ነው፡፡
ለዚህም ነው ለሀገራቸው ዳር ድንበር መከበር ሲሉ እድሜ ዘመናቸውን በፅናትና በቁርጠኝነት ላገለገሉ የኢትዮጵያ አየር ኃይል አባላት ተገቢው ክብር እንዲሰጣቸው፣ ታሪካቸውም ለትውልድ እንዲሸጋገር ማስቻል አስፈላጊ የሆነው፡፡ ኮሎኔል ባጫ ሁንዴም ከእነዚህ ጀግኖች አንዱ ሲሆን አስተዳደራዊ በሆነ ምክንያትና ቅሬታ ከሀገሩ ወጥቶ በመሰደድ በሰሜን አሜሪካ ውስጥ የብቸኝነት ኑሮ ሲኖር የነበረና ሕይወቱም እዚያው አልፎ እዚያው የተቀበረ፣ ገድሉና ጀግነቱ ጎልቶ የልተነገረ የኢትዮጵያ ኩራት ነው፡፡ ‹‹ክብር ለጀግኖቻችን›› ንቅናቄ እንደኮሎኔል ባጫ ያሉትን ጀግኖች ታሪክ አጉልቶ ለማውጣት የታቀደ ሲሆን በቅርቡም የኮሎኔል ባጫን አፅም ወደሀገሩ በማምጣት በተወለደባት፣ ባደገባትና ታላቅ መስዋዕትነትን በከፈለባት እናት ሀገሩ በክብር እንዲያርፍ የማድረግ እንቅስቃሴ ተጀምሯል፡፡

Subscribe & follow us on our YouTube and Rumble channels ON

https://www.youtube.com/channel/UC2A5SScyUj0P5LieInp-36A

https://rumble.com/c/c-1986332

Get in touch with your ETAFcommunity
https://etafclub.locals.com

Follow us

On Twitter - https://twitter.com/AyeleEshetu2

On Facebook - https://www.facebook.com/etafclub

Loading comments...