#ethiopian #defence #force Anthem with lyrics የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት መዝሙር Ethiopian Defense Force Song

3 years ago
17

https://www.youtube.com/c/Amba27
ሌሎች እዲደርስዎ አምባ ቲዩብን ሰብስክራይብ ያድርጉ
To receive other Subscribe to Amba Tube
#ethiopian #defence #force
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት መዝሙር
Ethiopian Defense Force Song
የኩሩ ህዝቦች መኖሪያ
***+++--------+++***
የኩሩ ህዝቦች መኖሪያ፤ የኅብረ ብሔር ቡቃያ
የሠላም ተምሣሌት ዓርማ፤የቀለሞች ኅብር ኢትዮጵያ
በደም አሻራሽ አትመው፤ህዝቦች ለሠጡን አደራ
ለህገ መንግስስታችን ክብር፤ታጥቀን ቁመናል በጋራ
የአበው የአርበኝነት ቅርስ፤ የነፃነት ገድል ፋና
ወደ ትውልድ ተሸጋግሮ፤ ወርሶት ፀንቷል እንደገና
ምድራዊ ፈተና በዝቶ፤ ዙሪያ ቢነድ በገሞራ
ጥሰነው እናልፈዋለን፤ የማይሞት ታሪክ ልንሰራ
ህዝብ ነው አያል ክንዳችን፤ሠላም ልማት ነው ቋንቋችን
የመፈቃቀድ አንድነት፤ እኩልነት ነው ዜማችን
የማንጨበጥ ነበልባል፤ እሳት ነን ለጠላታችን
ፍሙ ከርቀት ይፋጃል፤ ብረት ያቀልጣል ክንዳችን
ኢትዮጵያ በእኛ ደም ደምቃ፤ በአጽማችን ፍላጽ ተማግራ
እንደታፈረች እንድትኖር፤ ከዘመን ዘመን ተከብራ
ከመሞት በላይ እንሙት፤ ደማችን ሺህ ጊዜ ይፍሰስ
አየር አፈሯ ይባረክ፤ ምንግዜም ስሟ ይታደስ !!!
አየር አፈሯ ይባረክ፤ ምንግዜም ስሟ ይታደስ !!!
አየር አፈሯ ይባረክ፤ ምንግዜም ስሟ ይታደስ !!!

Loading comments...