TEDDY AFRO - ናዕት (እያመመው ቁጥር ፪) - [New! Official Single 2022] - With Lyrics

3 years ago
9

ናዕት (እያመመኝ መጣ ቁ.2)
-------------------------------
ግርም ያለ ጊዜ ሆነ ሰዓቱ
በዳንኪራው ደምቆ በምቱ
ለደቂቃም አይቆይ በስልቱ
ቦግ እልም እያለ መብራቱ
ቢጋርድ ሀሳብ አርጎ ሜዳን ገደል
እም አእላፍ ስቃይ ጭንቀት ቢደረደር
የነፍስ ሕላዊ መሻት ዋዌው ሳይገባቸው
ስንቶች በዘር ተዘፍቀው ታዘብናቸው
ዘውግ ያወረው ድንበር ማላውን የረሳ
ሳር ያለመልማል ዛሬም በእልፍ አእላፍ ሬሳ
እያረረ ሆዴ ብስቅ በማሽላ ዘዴ
ና ታደም ይለኛል ደግሞ በነ ኡኡ ሬጌ
ተላላ ዝንጉ ሰብ የሙታን ሸማ ደዋሪ
ምን አለ አይል ከፊት ሆኖ ቅርብ አዳሪ
ተናገር አፌ ደፍረህ ሳትናወጥ ከቶ
ዝም አይሆንም ሜዳ ተራራ ሞት መጥቶ
ከበሮ ግም ሲል በእምቢ ነጎድጓድ ምቱ
ይናዳል የዘር ድንዛዜ ያ ድውይ ቤቱ
ገለል በል ኤሳው ነፍሴን አንቀህ አታሳሳት
ብታገስ ባሰ ባንተ የልቤ እሳት
እያመመው መጣ
ያዳፈነው እሳት ከሆዱ ሳይወጣ
ልቤ እንደካቻምናው እያመመው መጣ
የሚያዜም ይመስላል ሲያጣጥር ተጨንቆ
ውስጡን ሲሰብቅለት ኡ….እያለ ማሲንቆ
ኡ….ኡ…..
እያመመው መጣ
የተረገጠ እውነት በጊዜ ውስጥ እግር
ታፍኖ የቆየ በሆታ ግርግር
ትንሽ ጋብ እንዳለ የጭብጨባው ጩኸት
እረጭ ሲል ውሸት ይናገራል እውነት
እያመመው መጣ
ቂምን ሻረውና ወይ ፍቅርን አንግሰው
ሁለት ሆኖ አያውቅም አንድ ነው አንድ ሰው
ከሐገርም ይሰፋል ያ የፍቅር ገዳም
መጠሪያው ሰው እንጂ ዘር አይደለም አዳም
ዶፍ ዶፍ ቢዘንብ እሳት
ሀገሬን ላልረሳት
ቃል አለኝ ኖሬ ሞቼም ልክሳት
ዳር አለው እንዴ ድንበር
ዳር አለው እንዴ
ዳር አለው እንዴ ፍቅር
የዘር ሐይማኖት ድንበር
ዳር አለው እንዴ ፍቅር
በዚህ ለፀና እውነት
የፍቅር ሐገር ከጥንት
ዘብ ያድራል ሁሉም እስከሞት
ዶፍ ቢዘንብ እቶን እሳት
ዶፍ ዶፍ ብዘንብ እሳት
አገሬን ላልረሳት
ቃል አለኝ ኖሬ ሞቼም ልክሳት
ናዕት

Loading comments...