Premium Only Content

ጡረተኛው የአሜሪካ ጦር ኮሎኔል | ምስጢሩን ሃቁን ተናግረዋል
#russia #ukraine #warzone #usa
በፎክስ ኒውስ ላይ ቀርበው ስለ ሩሲያ እና ዩክሬን ግጭት መንስኤ ምክንያት የሆነው እና ጦርነቱ ለምን እንደተፈጠረ እውነቱን ተናግረዋል።
ይህ ጦርነት በምዕራቡ ዓለም አነሳሽነት ከአሥር ዓመታት በላይ ሲታቀድ እና ሲጠነሰስ ቆይቷል።
በዚህ ጦርነት የተቀጠፉት ወደፊትም የሚቀጠፉት ህይወቶች ለእኛ በጣም ትልቅ እቅድ ላላቸው ልሂቃን የቼዝ ጨዋታ ተራ ወታደሮች ብቻ ናቸው።
ምናልባት አድማጭ ተመልካቾች ይህን ሃቅ የተናገረው ማክግሪጎር ምናልባትም ተመልሶ በፎክስ ኒውስ ላይ አይጋበዝም።
ወደ ቃለ-ምልልሱ እንሂድ
የፎክስ ጋዜጠኛ
የዩናይትድ ስቴት አፍ አሜሪካ መከላከያ የቀድሞ ከፍተኛ አማካሪ ኮሎኔል ዳግላስ ማክግሬጎር እዚህ አሉ። ስለተቀላቀሉን እናመሰግናለን።
የፎክስ ጋዜጠኛ ከመግቢያው በኋላ ወደ ጥያቄው ያመራል
👇
ፑቲን ይህን የሚያደርገው ለምን ይመስልዎታል? የመጨረሻ ትርፉስ ምንድነው?
ኮሎኔል ዳግላስ ማክግሬጎር ይመልሳሉ 👇
ቭላድሚር ፑቲን ቢያንስ ላለፉት 15 አመታት ሲያስጠነቅቀን የነበረውን ነገር እያከናወነ ነው ፣ ይህም የአሜሪካ ጦርንም ሆነ ሚሳኤላቸውን በድንበሩ ላይ ከተጠጉ እንደማታገስ ነው፣ እኛ የሩስያ ወታደሮችን እና የኩባ ሚሳኤሎችን የማንታገሰውን ማንችለውን ያህል።
እና እሱን ችላ አልነው ፣ በመጨረሻም እርምጃ ወሰደ። በምንም አይነት ሁኔታ ዩክሬን ኔቶን እንድትቀላቀል አይፈቅደም።
አሁን እየሆነ ያለው ነገር በምስራቃዊት ዩክሬን ጦርነት በእውነቱ ሊጠናቀቅ ጫፍ ደርሷሳ ፣ ሁሉም የዩክሬን ወታደሮች በብዛት እየተከበቡ እና እየተቆራረጡ ነው።
በደቡብ ምስራቅ ከ 30 እስከ 40,000 የሚደርሱ የዩክሬን ወታደሮች ክምችት አለ ፣ እና በሚቀጥሉት 24 ሰዓታት ውስጥ እጃቸውን ካልሰጡ ሩሲያውያን በመጨረሻ ያጠፏቸዋል ብዬ እገምታለሁ።
ለዚህም ነው ዜለንስኪ በተመሳሳይ ጊዜ ከፑቲን ጋር በተወካዮቹ በኩል እየተገናኘ ያለው ፣
ጨዋታው አልቋል እና ዜሌንስኪ ሊያገኘው በሚችለው ጥሩ ስምምነት ላይ መደራደር አለበት፣
እና ለዩክሬን ወገንተኝነት ማሳየቱ መልሶ ራሱን እንደሚጎዳው ለአሜሪካው ፕሬዝዳንት ነግረነዋል።
እናም ቭላድሚር ፑቲን ያንን ለምእራብ ዩክሬን ማለትም ከበላይኛው ወንዝ ማዶ ለዩክሬን እንደሚያደርግ አስባለሁ ነገር ግን ከጀርባው አሁን ባለበት ምስራቃዊ ክፍል፣ እዚያ ምን እንዳቀደ እርግጠኛ አይደለሁም፣ ሌላም ሪፐብሊክ ይመሰርታል ወይ የሚለውንም እርግጠኛ አይደለሁም?
ግዛቶቹ ቀጥሎ ወደ ሩሲያ ይገባሉ ምክንያቱም በታሪክ የሩሲያ ነው ፣ ነገር ግን ከዩክሬን በስተ ምዕራብ ያለው ግዛት የሩስያ አይደለም ፣ ያንን ያውቃል፣ እና እንደ ገለልተኛ ሀገር አብሮ በመኖር ደስተኛ ነው።
ጋዜጠኛው ጥያቄውን እንዲኽ ሲል ይቀጥላል 👇
እኔ የውትድርና ባለሙያ አይደለሁም። የጂኦግራፊ እንኳን ኤክስፐርት አይደለሁም ግን የፖላንድ ስር ጉያ ያለችውን ዩክሬንን ከወሰደ የኔቶ ሀገራት ይበቀሉታል፣ ስለዚህ ይኽንን ፑቲን የማይፈልገው ከሆነ። ታዲያ እሱ በናቶ አገሮች ላይ እስኪደርስ ድረስ መቀጠል የለበትም?
ኮሎኔል ዳግላስ ማክግሬጎር ይመልሳሉ 👇
ደግሜ ማለት እንዳለብኝ እገምታለሁ። ወደ ምዕራብ ወደ ፖላንድ ድንበር ለመሻገር ምንም ፍላጎት የለውም ፣ ከእነዚህ ድርድሮች ውስጥ የምታገኙት ይመስለኛል፣
እሱ ያንን ግዛት በኦስትሪያ ወይም ባለቀው ባለው ሞዴል ላይ ለመተው በጣም ፈቃደኛ ነው።
አሁን ሩሲያ ኢስቶኒያን እና የላትቪያ ክፍልን ስትነካ በእርግጥ ሩሲያ ሊትዌኒያንም ትነካለች።
ከእኛ ጋር ጦርነት የመግባት ፍላጎት የለውም፣ እናም ለዚህ አላማ በጣም ትንሽ የሆነ ሰራዊት አለው፣ ኢኮኖሚውም ከደቡብ ኮሪያ ያነሰ መሆኑን ያውቃል።
ስለዚህ ይህ እሱ የሚፈልገው ነገር አይደለም። እርሱን በአገሩ ሴጣናዊ ለማድረግ በምናደርገው የተለመደ ጥረት ማድረግ ወደ ማይፈልገው ነገር እያስገባነው ነው።
ማስታወስ ያለብን ዩክሬን ከ 158 የአለም ሀገራት በሙስና ቀዳሚውን ትይዛለች፣ ሩሲያ ምናልባት 3 ወይም አራት ከፍ ብላ በላያቸው ላይ ትገኛለች ፣
ይህ ሁሉም እንደሚናገረእ የሊበራል ዲሞክራሲ አንፀባራቂ ምሳሌ አይደለም ።
ከዚኽም በራቀ ፣ ሚስተር ሱሊንስኪ ጋዜጠኞች እና የፖለቲካ ተቃዋሚዎቹን ያስራል ።
ከዚኽ መራቅ ያለብን ይመስለኛል።
የአሜሪካ ህዝብ ከዚኽ መራቅ አለብን ብለው ያስባሉ። አውሮፓውያን ከዚኽ መራቅ እንዳለብን ብለው ያስባሉ ፣
እናም የጦር መሳሪያዎችን ማጓጓዝ እና ዩክሬናውያን እንዲሞቱ ማበረታታትን ማቆም አለብን ፣ እና ይኽ ተስፋ የለሽ ጥረት ምንድነው?
የፎክስ ጋዜጠኛ ጥያቄውን በመቀጠል ይሰነዝራል 👇
ስለዚህ ከሱ መራቅ አለብን ሲሉ ማዕቀብ አይኑር፣ ወታደራዊ እርዳታ አይኑር ፣ ሩሲያ ልትወስደው የምትፈልገውን የዩክሬን ክፍል ትውሰድ ማለት ነው?
ኮሎኔል ዳግላስ ማክግሬጎር ይመልሳሉ 👇
አዎ፣ በፍፁም፣ ለዓመታት ሲናገሩት በነበረው ጉዳይ ከሩሲያውያን ጋር የምንጣላበት ምንም ምክንያት አይታየኝም።
ዝም ብለን ችላ ማለትን መርጠናል፣
እና ከሁሉም በላይ ደግሞ፣ እዚያ ያለው ህዝብ ከራሳቸው የማይለይ ነው።
ታውቃላችሁ፣ በጣም የሚያስጨንቀው ነገር በአንድ በኩል ኃይላችንን ወደ ጦርነት አንልክም፣ ነገር ግን ዩክሬናውያን በማጣደፍ በጦርነት ውስጥ ያለ ጥቅም እንዲሞቱ እናሳስባለን።
ማሸነፍ አይችሉም።
ካላቆመ ፣ እስካሁን ካየሃቸው ነገሮች ሁሉ የከፋ የሰብአዊ አደጋ እንፈጥራለን።
ስለተቀላቀሉን እናመሰግናለን።
-
LIVE
Steven Crowder
1 hour ago🔴Minnesota Catholic School Shooting Update - Shooter & Manifesto
34,459 watching -
LIVE
The Jimmy Dore Show
53 minutes agoTrump & Newsom Trade Barbs Over HAND SIZE! Cracker Barrel CAVES to Public Pressure!
2,005 watching -
LIVE
Darkhorse Podcast
1 hour agoThe 291st Evolutionary Lens with Bret Weinstein and Heather Heying
194 watching -
LIVE
StoneMountain64
2 hours agoHUNTING FOR THE FIRST WIN BACK ON WARZONE
243 watching -
1:13:02
Simply Bitcoin
3 hours ago $1.51 earnedINSIDER CONFIRMS 1M Bitcoin Buy INCOMING!! | EP 1319
33.9K -
1:03:00
Sean Unpaved
2 hours agoCFB Deep Dive: Matt Moscona's Expert Takes on the Gridiron
27.9K -
27:39
Crypto.com
1 day ago2025 Live AMA with Kris Marszalek, Co-Founder & CEO of Crypto.com
99.6K6 -
LIVE
SternAmerican
23 hours agoElection Integrity Call – Wed, Aug 27 · 2 PM EST | Featuring Arizona
290 watching -
1:00:05
Timcast
2 hours agoMASS SHOOTING At Catholic Church In Minneapolis, Children Reportedly Targeted
154K81 -
1:34:01
Tucker Carlson
1 hour agoChristopher Caldwell: Is It Too Late to Save the English-Speaking World?
31.3K41