እውነተኛው የአፍሪካ ግዝፈት መጠን | የ500 ዘመኑ ሃሳዊ የዓለም ካርታ AFRICA | ETHIOPIA | nomore

2 years ago
4

#Tuka_Mathiwos #worldMap #
እውነተኛው የአፍሪካ ግዝፈት መጠን - የዓለም ካርታዎች ከ500 ለሚበልጡ ዓመታት ቀጣፊ-አሳሂ ነበሩ ?

(ቱካ ማቲዎስ)

ካስተማሩህ ትምህርት የትኛውም እውነት አልነበረም ። ለዛም ነው ማልኮም ኤክስ " ልጆቹ በጠላቱ እንዲማር የሚፈቅድ፣ ሞኝ ብቻ ነው"
" Only a fool let his enemy educate his children " ያለው

ሉሙምባ ደግሞ "አፍሪካ የራሷን ታሪክ ትጽፋለች ፣ በሰሜን ፣በደቡብም የክብር እና የማሸነፍ ታሪክ ይሆናል" ብሎ ትንቢታዊ ቃል ተናግሮ ነበር።

ይኽ መፈፀሚያው ጊዜ አሁን ነው ፣ የውሸት ተረኩን የመቀየሪያ ትክክለኛ ወቅት።

የአፍሪካን ባህል ፣ ማንነት፣ ቅርስ ፣አንጡራ ሃብትና ንብረት ከመዝረፍ በተጨማሪ አፍሪካን ለማጠልሸት ለማሳነስ ከተፈበረኩ የውሸት ፈጠራዎች መካከል 👇

እንደምሣሌ:- ብናነሳ "የአፍሪካን ጥንታዊ ቀደምት ሥልጣኔ ጀማሪነት እውነት" ደብዛ ለማጥፋት በግብጽ በቁፋሮም ሆነ ቆመው በሚገኙ የፈርኦን እና ጥንታዊ ሰዎች ላይ የሚፈፅሙት አሳፋሪ ተግባር አለ👇

ይኽም የሃውልቶቹን አፍንጫ በመጉመድ የሃውልቱን ጥቁር ማንነቱን ማሳጣት እና እነሱን እንዲመስል ማድረግን የመሰለ የዥል ተግባር ይፈፅማሉ ፣
ልብ ያላሉት ነገር አፍሪካ ደፍጠጥ ያለ አፍንጫ ብቻ ሳይሆን ሰልካካ አፍንጫም ባለቤቶች እንደሆንን ነው።
(ይኽን ጉዳይ ሌላ ጊዜ በሰፊው እምንመለስበት ይሆናል)

ከነዚኽ መሰረታዊ ለውጥ ከሚያስፈልጋቸው ሆን ተብለው አፍሪካ ላይ በተቀናጀ መልኩ ከሚፈፀሙ ተግባሮች አንዱ ዛሬ ላነሳላችኹ የወደድኩት
አፍሪካ ያልሆነችውን እንደሆነች የሚያሳየውን የዓለም ካርታ ጉዳይ እንይ 👇

እስካሁን የምታውቁት ፣ ትምህርት ቤትም መምህራኖቻችኹ ያሳዩአችኹ ፣ ምናልባትም በእጃችኹ ያሉት ፣ ለልጆቻችኹ ማስተማሪያ ብላችኹ በቤቶቻችኹ ግድግዳ ላይ የሰቀላችኹት በጠረጼዛችኹ ላይ ያስቀመጣችኹት ሉል እና የዓለም ካርታ ፍፁም ሃሰት ነው።

ዓለምን እነሱ ከነገሩን ካሳዩን ፍፁም በተቃራኒው በትክክለኛው እይታ ስናያት 👇

  አፍሪካ ከአውሮፓ፣ ቻይና እና ዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ ከኹሉም በመጠን በግዝፈት ትበልጣለች።

ነገር ግን በአብዛኛዎቹ አኹን እየተጠቀምንበት ባሉት የአለም ካርታዎች ላይ አፍሪካ በዝቅተኛ መጠን ትወከላለች።

እውነታው ግን ምንድነው?

* የአፍሪካ ጠቅላላ ስፋት   = 30,37 ሚሊዮን ኪ.ሜ ስክዌር

* የቻይና ጠቅላላ ስፋት     =  9.6 ሚሊዮን ኪ.ሜ ስክዌር

* የአሜሪካ ጠቅላላ ስፋት = 9,8 ሚሊዮን ኪ.ሜ ስክዌር

* የአውሮፓ ጠቅላላ ስፋት = 10,18 ሚሊዮን ኪ.ሜ ስክዌር

አንዳንዶች "ይህ በዘረኝነት ላይ የተመሰረተ ነው" ይላሉ። ሌሎች ደግሞ "የአኅጉሮችን እና የአገሮችን ስፋት በአማፕ በትክክል መወከል አይቻልም" ይላሉ።

ንድፈ ሃሳቡ ምንም ይሁን ምን፣ እውነታዎች እውነታ የማይለወጥ ሃቅ ሆነው ይቆያሉ ፣ ማጭበርበር ማታለል አይቻልም ።

አፍሪካ ግዙፍ፣ ሀብታም እና እያበበች ያለች ወደ ቀደመ ኃያልነቷ ክብሯ በንቃት እየሄደች ያለች አህጉር ናት ።

የሚገርመው ነገር፣
እስያ ከፍተኛ የህዝብ ቁጥር ያላት አህጉር መሆኗን በኩራት እንደ ታላቅ እድል ያዩትና ወደ አፍሪካ ሲመጡ 👇
"በአፍሪካ እየጨመረ ያለው የህዝብ ቁጥር ስጋት እና አሳሳቢ ነው" ይላሉ
ይኽንንም ለመቆጣጠር ውርጃ የወሊድ ቁጥጥር እንድናደርግ በእርኩስ-ተራድዎ ድርጅቶቻቸው ክኒኑንም እንድንውጥ ፣ ከተፈጥሮ ውጭ እንድንሆን ፣ መከላከያ መቆጣጠሪያ እያሉ ፕሮጀክት ቀርፀው ሕዝባችንን እንድንቀንስ ይለፉልናል ይጥሩልናል።

ምናልባት እንደእኔ "የስነ ሕዝብ ቁጥር ስታቲስቲክስ" እንዲሁ ሕዝቡን ለማታለል አዘጋጅተውት ይሆናል ብዬ አስባለኹ። ትክክለኛ አድሏዊ ያልሆነ ቆጠራ ቢደረግ አፍሪካ በመልክአ-ምድራዊ ግዝፈት ብቻ ሳይሆን በህዝብ ቁጥርም ከዓለም ሳትበልጥ እንደማትቀር ማሳያዎች አሉ።

ከአፍሪካ እንሻላለን ብለው እኛን “የሦስተኛው ዓለም አህጉር” በማሳነስ ቢሉንም ፣ ሀብታቸውን ሁሉ አፍሰው አፍሪካን ለመናድና ለማጥፋት ወይም በዳግም ወረራ ለመቀራመት ግን እንቅልፍ እየወሰዳቸው አይደለም።

አፍሪካ በዓለም ካርታ ላይ አንሳ መገለጿን እውነታ መግለጽ ለምን አስፈለገ ፣ ጥቅሙስ? የሚል ጠያቂ አይጠፋም 👇

ምክንያቱም ተረኮች ግንዛቤን ይቀርፃሉ ፣ ግንዛቤ እርምጃን ያስከትላሉ።

#eurocentric_maps ወይንም አውሮፓውያንን ማዕከል ያደረገው የዓለም ካርታ እውነታዎችን በብዙ መልህ አዛብተዋል።

አሁንም አሜሪካ በካርታዎች እና ግሎብስ ላይ እንደሚታየው ትልቅ ነው ብላችኹ ታስባላችኹ?
ነገሮች እንዳየናቸው የሚመስሉትን ያህል ትልቅ አይደሉም፣

ይህ በአዕምሯችን የአእምሮ ሒሳብ ክፍል ውስጥ ያለን ሥር የሰደደ መጥፎ መረጃ ክምችት ብቻ እንጂ እውነታው ሌላ ነው።

እኛ አፍሪካውያን በአእምሯችን ላይ በመጥፎ የሳሉብን እና ሥር የሰደደ እነሱ ሰጥተውን እኛም ተቀብለን የያዝናቸው የዓለም ካርታዎች በእጃችን አሉ ። እያልኩ ያለኹት "እነዚኽን ቀጣፊ የዓለም ካርታዎች ለታሪክ እንደቀመጡ ስለምንፈልግ ቦጫጭቀን ባንቀዳድዳቸውም መለወጥ ግን አለብን"

ከሌሎች አገሮች አንጻር የአፍሪካን ትክክለኛ መጠን የሚያሳይ በ ካይ ክራውስ ( Kai Krause ) የተዘጋጀው የዓለም ካርታ የመረጃ ንድፍ ነው።

በብዛት ጥቅም ላይ የዋለው የዓለም ካርታ ትንበያ  እ.ኤ.አ በ 1569 በፍሌሚሽ ካርቶግራፈር ጄራርደስ መርኬተር #Gerardus_Mercator የተነደፈው ለአሰሳ ነበር።

እንደ አለመታደል ሆኖ፣ የመርኬተር የዓለም ካርታ ትንበያ ወደ ዋልታዎቹ የሚቀርቡትን የመሬት ሃገራት ወይም አኅጉራት ስፋት መጠን እና ቅርፅ በእጅጉ ያዛባ ሲሆን ይህም ከትክክለኛቸው የበለጠ መጠን እና ስፋት ያላቸው እንዲመስሉ አድርጓቸዋል ።

ምድር ክብ ናት።

  የማንኛውም የዓለም ካርታ ፈተና ክብ ምድርን በጠፍጣፋ መሬት ላይ መወከል ነው።

አፍሪካ በአለም ካርታዎች ላይ ከሚታየው በላይ ትልቅ ነች! እጅግ በጣም ግዙፍ !!

{እዚኽ ሊንክ ውስጥ የምታገኙት አስገራሚ ማስረጃ የአፍሪካን ትክክለኛ መጠን ከሌሎች የዓለም ዋና ዋና አገሮች ጋር ባለው ግንኙነት በተጨባጭ ያሳያል።}

እውነት የሆኑ የሚመስሉ  በተለምዶ የምንጠቀማቸው የዓለም ካርታዎች ትክክለኛነት "ልብ ወለድ" ፈጠራ እንጂ ሌላ አይደለም።

ከዚህ በታች ያለው ማነፃፀሪያ የአፍሪካን ስፋት ትክክለኛ እይታ እና የአለም ካርታ መጠኑን እንዴት በተሻለ መልኩ እንደሚያንጸባርቅ እናይበታለን። 👇

ካርታው የሚያሳየን (30,3 ሚሊዮን ኪሜ²) ስፋት ያላች አፍሪካ 👇

👉 ከቻይና (9,6 ሚሊዮን ኪሜ²)
👉ከዩኤስ (9,4 ሚሊዮን ኪሜ²)፣
👉 ከምእራብ አውሮፓ (4,9 ሚሊዮን ኪሜ²) ፣
👉 ከህንድ (3,2 ሚሊዮን ኪሜ²) ፣
👉አርጀንቲና (2.8 ሚሊዮን ኪሜ²) እና
👉ሌሎች ሶስት የስካንዲኔቪያ አገሮች እና የብሪቲሽ ደሴቶች
ውህደት አንድ ላይ ሆነው እንኳን እንዴት አፍሪካ በስፋት እንደምትበልጥ ያሳያል።

እውነተኛው እና ትክክለኛው የአለም ካርታ (አረንጓዴው ንድፍ) እና በጂኦግራፊ ትምህርት ለዓመታት የተማርነው (ጥቁር ንድፍ) ማነፃፀሪያዎች ናቸው 👇
{ምስሉን በዚኽ ሊንክ ታገኙታላችኹ}

❗እባካችኹ እዚኽ ሊንክ ላይ ገብታችኹ በደንብ ተመልከቱ ማነፃፀሪያውን❗ የአንዳንድ አገሮች መጠን ጨምሯል ፣ መላው የአፍሪካን አህጉር ግን በጣም ትንሽ እና ከሃገሮች እንኳን አሳንሰውታል።

#NoMore

(ነጽሩ ወዘሠናየ አጽንዑ)

#africamap #worldmap

Loading comments...