መና | Manna | ከሠማይ የወረደው ምስጢራዊ ምግብ ምንድነው? | አሁንስ የት ይገኛል? | ሳይንሱ ስለዚኽ ተሃምር ምን ይላል? Part - 1

2 years ago
52

What did Israel eat in the wilderness?
christian religion
bible wisdom
christian story
old testament
bible exodus
exodus 16
manna bible
quail bible
moses exodus
Manna
What is manna?
manna meaning
manna from heaven meaning
ሙዳዬ መና
EOTC

#Manna
#What_is_manna?
#What_did_Israel_eat_in_the_wilderness?
What is it?
#Exodus
Wilderness journey
Wilderness of Sin
Marah
Elim
by the Red Sea
Canaan
Bible
God
Jesus
Jesus Christ
Bible Study
Bible Lesson
Bible Lecture
Bread of Life
Daily Bread
Give us this day our daily bread

እንደምን አላችኹ?! የቱካኤል ቻናል አድማጭ ተመልካቾች ፣
ሠላማችኹ በያላችኹበት ኹሉ ይብዛላችኹ!

በዚኽ ፕሮግራማችን በመጽሐፍ ቅዱስ ስለተጠቀሰው እስራ"ኤላውያን በበረሃ ሳሉ ከሰማይ እየወረደላቸው ይመገቡት ስለነበረው "መና" ወይም በሌላ መጠሪያው "የመላእክት ምግብ" ስለሚባለው ድንቅ ነገር እናነሳለን።

  ይኽ ጉዳይ ፣ የአንዳንዶች "መከራከሪያ" የሌሎች ደግሞ "ጥያቄ" የሆነ ሃሳብ በመሆኑ እኛም በቻልነው ኹሉ የደረሰንበትን ማስረጃ እና መረጃ በማቅረብ ለመመለሥ እንሞክራለን።

ጽሑፉን አሰናድቼ የማቀርብላችኹ ቱካ ማቲዎስ  ነኝ አብራችኹኝ ቆዩ

#ከሠማይ_የወረደው_ምስጢራዊው_ምግብ {{መና}} ምንድነው? አሁንስ የት ይገኛል? ሳይንሱ ስለዚኽ ተሃምር ምን ይላል?

የገነት እንጀራ / የሰማይ እንጀራ ፣ የመላእክት ምግብ  ከአራቱ የፍጥረታት መሰረቶች ማለትም (ከውሃ፣ከአየር፣እሳት፣አፈር) ውጪ ያለ አምስተኛው ምስጢራዊው ንጥረ ነገር ይባላል።

✔✔✔✔✔✔✔✔✔✔✔✔✔✔✔✔✔✔✔✔

👉መና ከሰማይ የወረደበት ምክንያት ምንድነው?

በዘፀሐት ጊዜ እስራኤላውያን በሲን በረሃ ሳሉ "ራበን አሉ" ይለናል መጽሐፍ ቅዱስ

ዘፀ ፲፮÷፫ "....በራብ ልትገድሉ እኛን ወደዚኽች ምድረበዳ አውጥታችኻል፣ በሥጋው ምንቸት አጠገብ ተቀምጠን እንጀራ ስንበላ ስንጠግብ ሳለን በግብጽ ምድር በእግዚአብሔር እጅ ምነው በሞትን አሏቸው።"

ዘፀ ፲፮÷፬ "እግዚአብሔርም...እንሆ እንጀራን ከሰማይ አዘንብላችኃለሁ...የሚበቃቸውን ይልቀሙ"

#የስሙ_ስያሜ

ዘፀ 31 "...ስሙን መና ብለው ጠሩት።

ምናልባት በኛ ቋንቋ #መና ሲጠብቅ በረከት፣ስጦታ ድንገት የሚገኝ አዱኛ ይሆናል። ሲላላ "መና" ባዶ መቅረት፣ኃብት አጠራቅሞ ድንገት ማጣትን ለመግለጽ " መና ቀረሁ" መባሉ ከዚህ ምስጢራዊ ምግብ ጋር ተያይዞ የመጣ ሳይሆን አይቅርም።

እንግሊዝኛው Manna ይለዋል ይኽውም marriam-Websrmter መዝገበ ቃላት ሲፈታው "usually sudden & unexpected source of gratification,plasure or gain" ይለዋል ከኛ ጋር ተዛምዶ አለው።

ዘፀ ፲፮÷፲፭ "...ባዩት ጊዜ ያ ምን እንደሆነ አላወቁምና ርስ በርሳቸው #ይኽ_ምንድር_ነው? ተባባሉ " በዚህም "what's it?" "ምንድርነው?" "Manna" አሉት የሚሉ አሉ።

መና አማርኛ
መና (ህብስተ-መና) ግእዝ፣
ማና (መና) ትግርኛ
Ma'n Hu እብራይስጥ

በብዙ ቋንቋዎች ኦሮምኛን ጨምሮ "ማል? ማሊ?  ምንድር ነው ማለት እንደሆነ የታወቀ ነው።

ምግብ ፣ mile ፣ manna የሚባሉ ቃላትም መብልን የተመለከተ ትርጉም አላቸው።

#መና_ንጥረ_ነገሩ_ምንድነው?

ዘፀ ፲፮÷፲፩ "...ማንጎራጎር ሰማሁ...ወደ ማታ ሥጋን...ማለዳም እንጀራን ትጠግባላችሁ።"

እዚህ ላይ #ሥጋ እና #እንጀራ ተብሎ የተገለፀ ቢመስልም ወረድ ብሎ ግን...

፲፫ "እንዲህም ሆነ በመሸ ጊዜ ድርጭቶች መጡ ፣ ሰፈሩንም ከደኑት ፣ ማለዳም በሰፈሩ ዙሪያ ጠል ወድቆ ነበር።

{ወደ ማታ ሥጋን ያለው ድርጭቶችን መግቧቸው ነው።(ስለ #ድርጭት በሚቀጥለው ክፍል ትንሽ እናወራለን) ፣ ማለዳም እንጀራን ያላቸው ሲነጋና ጠሉ ሲያልፍ #መና አግኝተዋል።}

፲፬ " የወደቀውም ጠል ባለፈ ጊዜ እነሆ በመሬት ላይ እንደ ደቃቅ ውርጭ ኾኖ ቅርፊት የሚመስል ደቃቅ ነገር በምድረ በዳ ታየ"

#የመና_መልክና_ዓይነቱ?

ዝፀ 31 "ርሱም እንደ ድንብላል ዘር ነጭ ነው።

ዘኍ ፲፩÷፯ " ...እንደ ድንብላል ዘር ነበረ።መልኩም ሙጫ ይመስል ነበር።

#ጣዕሙ

ዘፀ 31 "....ጣዕሙም እንደ ማር ቂጣ ነው።

ዘኍ ፲፩÷፰ "...ጣዕሙም በዘይት እንደተለወሰ እንጎቻ ነበረ።"

ይለናል ይኽም ለሰው ልጆች ከሚያውቁት የተለየና እንግዳ ነገር መሆኑንና እጅግ ደቃቅ ምናልባትም ድንብላል ያኽል መጠን ያለው እንደሆነ መረዳት ይቻላል።

፲፭ "...ባዩት ጊዜ ያ ምን እንደሆነ አላወቁምና...ይኽ ምንድር ነው? ተባባሉ

#አንባቢ_በርትተህ_እንድትከተለኝ_ይሁን!
#እባክህ??

#የመላእክት_እንጀራ የተባለው መና #ሰለቸን_አንበላም ያሉ ምን ሆኑ?
[ክፍል ፪]
(ቱካ ማቲዎስ)

#መናውን_ከለቀሙ_በኃላ_አዘገጃጀቱ?

ዘኍ ፲፩÷፰ "...በወፍጮም ይፈጩት ፣ በሙቀጫ ይወቅጡት ነበረ።በምንቸትም ይቀቅሉት ነበር።እንጎቻም ያደርጉት ነበር።"

ዘፀ ፲፮÷23 "...የምትጋግሩትን ጋግሩ ፣ የምትቀቅሉትንም ቀቅሉ..."

#ከሠማይ_አወራረዱ?

በጠል አማካኝነት ለሊት እንደሚወርድ ተፅፏል።

ዘኍ ፲፩÷፱ "...ሌሊትም ጠል በሰፈሩ በወረደ ጊዜ መናው በላዩ ይወርድ ነበር።

መዝ 78÷23 "ደመናውንም ከላይ አዘዘ፣የሰማይንም ደጆች ከፈተ፣ይበሉም ዘንድ መናን አዘነበላቸው፣የሰማይንም እንጀራ ሰጣቸው።"

"የማታ ሲሳይ/እንጀራ ስጠኝ" የሚባለው ከእድሜ በተጨማሪ በዚኽም ምክንያት ይሆን?

እስራኤላውያን ለስንት ዓመታት በሉት?
ዘፀ 35 "...አርባ ዓመት መና በሉ።ወደ ከነዓንም ምድንበር እስኪመጡ ድረስ..."

መዝ 78 ÷25 "የመላእክትንም እንጀራ ሰው በላ ሥንቅንም እስኪተርፋቸው ላከላቸው" ይኽን እየበሉ ቢጓዙም ቅሉ....

በመንገዳቸው መካከል ድጋሚ እንዳጉረመረሙና መና መብላት እንደሰለቻቸውም መጽሐፍ ይነግረናል።

ዘኍልቁ ፲፩ ÷፬-፭ "...የምንበላውን ሥጋ ማን ይሰጠናል?በግብጽ ያለ ዋጋ እንበላው የነበረውን ዓሣ፣ዱባውኑም፣....ቀዩንም ነጩንም ሽንኩርት እናስባለን።

፮ "...ሰውነታችን ደረቀች።ዓይናችንም ከዚህ መና በቀር ምንም አታይም አሉ።"

በዚህም ለስጋ አምሮታቸው የምሥራቅንና የደቡብን ንፋሳት አስነስቶ መሬትን አንድ ክንድ እስኪሸፍን ሥጋና #ድርጭት ተልኮላቸው ሊበሉ ሲሉ እንደተቀጡ {ዘኍ 31-34} እና መዝ 78÷26 ይነግሩናል።

#ድርጭት _ምንድርናት?
ከእርግብ ምታንስ ወፍ ናት፣ሥጋዋ ድርብርብ።

ባልታጨደ ጤፍ ውስጥ ትኖራለች።
የገጠር ሰው ድንገት ሳይታሰብ ከእግር ስር ወይም ከአንድ ሌላ ቦታ ብርርር ብላ ስለምታስደነግጥ ድርቂት ይሏታል (ድር ብር ብላ ድንገት አስደንግጣ ክው፣ድርቅ ታደርጋለችና። አድርቅ ናት ሲሉ ድርጭት ያሏት ይባላል።

በጥጋባቸው የሰማዩን ምግብ ናቁ አጉረመረሙ ለዓይንም እስኪታክት የዓሣና የድርጭት ሥጋ ክምር ለቅጣት ተሰጣቸው።

ይኽውም በእጅ የያዙትን ንቆ አጉል መጎምዥትና ምኞት፣ የተመኙትን አግኝተው ሳያጣጥሙ ወደ መቃብር እንደሚያወርድ ትልቅ ትምህርት የሚሰጥ ነው።

መና የተባለው ይኽ ምግብ የሥጋ ብቻ ሳይሆን የነፍስም እንደሆነ ዳዊት በመዝሙሩ ይነግረናል

መዝ 78÷ 18-20 "ለነፍሳቸው መብልን ይፈልጉ ዘንድ በልባቸው እንዲህ ብለው ፈተኑት...እግዚአብሔርን እንዲህ ብለው አሙት...በምድረ በዳ ማዕዱን ያሰናዳ ዘንድ ይችላልን?...እንጀራ መስጠትስ ይችላልን?"

ራዕ ፪÷፲፮-፲፯ "በአፌም ሰይፍ እዋጋቸዋለኹ...ድል ለነሣው ከተሰወረ መና እስጠዋለሁ..."

#አንባቢ_በርትተህ_እንድትከተለኝ_ይሁን!!
#እባክህ??

--------- #ይቀጥላል ------------

(ነጽሩ ወዘሠናየ አጽንዑ)

Loading comments...