Premium Only Content

የዱር ውሾች አሳድገው | ለአቅመ ሄዋን ያደረሷት | Oxana Malaya
በምድራችን ላይ የሠው ልጆችን የዱር ወይም የቤት እንስሳት አሳድገዋቸው የእንስሶቹን የአኗኗርና አመጋገብ ዘይቤ ወርሰው፣ የሠውን ማኅበራዊ አኗኗር ልማድ ትተውና ረስተው እንደ ዝንጀሮ፣ እንደ ዶሮ፣ እንደ ተኩላ ወ.ዘ.ተ ሆነው ያደጉ ሰዎች እንዳሉ የታወቀ ነው።
እስካሁንም በዚኽች ድንቃድንቋ በማያልቀው ዓለማችን ከ100 በላይ በሕፃንነታቸው ተትተው ወይም ተጥለው ከሰዎችም ተነጥለው በተለያዩ እንስሳት እንክብካቤ ተደርጎላቸው በዱር ያደጉ ወይም ማንም ሳያገኛቸው ብቻቸውን የኖሩ ሰዎች በጥናት መገኘታቸው ይገለፃል።
ለምሣሌ:- ታሪክ ከማይረሳቸው ውስጥ ሮማን ኢምፓየር 753 BC የመሰረቱት ሁለቱ መንትያ ወንድማማቾች #Remus_እና_Romulus የዱር ተኩላ ጡት አጥብታ እንዳሳደገቻቸው ይነገራል።
ለዚኽም Lupa Capitoline (Capitoline wolf) የሚል ሁለቱ መንትዮች የተኩላዋን ጡት እየጠቡ የሚያሳይ በሮማ ከተማ አቅራቢያ የነሃስ ኃውልት እስካሁን ቆሞላቸዋል።
{ ይኽን እንደ ምሣሌ በጥቂቱ ያነሳነውን ታሪክ ሌላ ቀን በሠፊው እንመለስበታለን።}
ይኽን አስገራሚ መረጃ ያዘጋጀልን ቱካ ማቲዎስ ...ሲሆን
ጽሁፉን የማቀርብላችኹ እኔ ኤደን አስማማው ነኝ
አኹን በዘመናችን ስለተደረገ አስገራሚ እንግዳ የሆነ ድርጊት ለማመን የሚከብድ ግን እውነተኛ ታሪክ ወደሆነ ክስተት እንሂድ።
የዮክሬናዊቷ Oxana Malaya አስገራሚ ታሪክ ሚጀምረው ገና የ3 ዓመት ጨቅላ እያለች ነው። ወላጆቿ በአደንዛዥ እፅ የናወዙ በአልኮል ሱስ የተለከፉ ነበሩ።
ከዕለታት በአንዷ እራሳቸውን በሳቱባት ምሽት (ምናልባት እያለቀሰች አስቸግራቸው ይሆናል) ከቤታቸው ውጪ አውጥተው ይዘጉባታል።
የ3 ዓመቷ ሕፃን ለምሽቱ ብርድ ማስታገሻና መሸሸጊያ ፍለጋ ትናንሽ እግሮቿ ወደመሯት ተጓዘች።
በጉዞዋ ያጋጠማት የሰዎች ቤት ሳይሆን የዱር ውሾች መሸሸጊያ፣ዋሻና ጎሬ ነበር።
በዋሻው ውስጥ የሚኖሩ የውሾች መንጋ በድንገት በእንግድነት በተገኘችው የሰው ልጆች ሕፃን ልጅ ስጋት፣ ፍርሃት፣ ድንጋጤ ሳይሰማቸውና ሳይተናኮሏት በተቃራኒው ርህራሄና ደግነት አሳይተው በጉዲፈቻ አይነት የመንጋቸው አንድ አካል አድርገው ያሳድጓታል።
በጠፋችበት ምሽት፣ ማንም የአካባቢው ሰው ለቅሶዋን አስተውሎ ወደየት? እንዳመራች ያያት የለም። ወላጆቿም ሊፈልጓት አልፈለጉም ወይም ግድም አልሰጠቻቸው ይሆናል።
ሕፃኗ Oxana Malaya ከውሾቹ ጋር ጥሬስጋ እየተመገበች፣ የጠጡትን እየጠጣች እንደሆኑት እየሆነች፣ ቀናት ቀናትን፣ ወራት ወራትን እየወለዱ ዓመታት ሲተኩ ልክ እንደ ውሻ ከውሾቹም መንጋ እንደ አንዷ ሆና አረፈችው።
ከዋሻቸው ሲወጡ ልክ እንደነሱ " በአራት እግሯ " (በእጅና እግሯ) እየተራመደች፣ እየዘለለችና እየሮጠች አብራቸው መውጣት ጀመረች።
ነገረ ሥራዋ ሁሉ እንደውሻ ሆነ።
ልክ እንደ ውሻ ቡችላ ጥበቃ እያደረጉላት፣ እሷም ምላሷን እንደውሻ እያወጣች እያለከለከችና እየተቁነጠነጠች ስር ስራቸው ትላለች።
ልክ እንደነሱ ከወንዝ፣ከኩሬ፣ ከሚፈስ ቧንቧና ቦይ ወደ ዋሻውም ከሚመጣ ወራጅ ውሃ በምላሷ እየጠጣች፣ ውሃ ሰውነቷን ሲነካት ልክ ውሾች ለማራገፍ እንደሚያደርጉት አንገቷን እየነቀነቀች፣ ሰውነቷን የማርገፍገፍ እንቅስቃሴ ታደርጋለች።
ውሾች ለፅዳት ምናቸውን ይጠቀማሉ? ምላሳቸውን አይደል! እሷም ከእነሱ እንደ አንዷ ናትና ይኽንኑ የፅዳት ተግባር ታከናውናለች።
ሰው የውሻን ጩኽት ለማስመሰል የሚጮኽውን ጩኽት አይነት ሳይሆን ትክክለኛ፣ ጠንካራና ኃይለኛ ከውሾች መለየት የማይቻል የውሾች ጩኽት ትጮኻለች።
የውሾች መንጋ አንዷ ቤተሰብ ሆና ያደገችው የOxana መጨረሻ
Oxana በውሾች መንጋ መካከል እንደ ቡችላቸው ቆጥረው አሳድገው፣ምግብ፣መጠጥና መጠለያ ከጥበቃ ጋር ሰጥተው በጫካውና ከደኑ አጠገብ ከሚኖሩት በዩክሬን ገጠራማ አካባቢ ገበሬዎች ጋር እንዴት በዘዴ መኖር እንደሚቻል አስተምረዋታል።
አልፎ አልፎ ሰው ማየቷ ባይቀርም ያሳደጓትን ቤተሰቦቿን መንጎች ውሾቹን መርጣ ትኖራለች።
ከዘሮቿ የሠው ልጆች የሚያገናኛት ቋንቋ፣ የአረማመድ ሁኔታ፣ እንቅስቃሴ ድርጊት ሁሉ ልዩ በመሆኑ እንደ ተመራማሪዎች ገለፃ "እንስሳ በሰው ገጽታ" የሚል ስያሜ አሰጥቷታል።
ከ6 ዓመታት "ውሻነት" በኃላ አንዲት የአካባቢው ነዋሪ "ከዱር እንስሶቹ መካከል አንዲት ሕፃን ልጅ አብራቸው ስትንቀሳቀስ በተደጋጋሚ ማየቷን" ለፖሊስ ሪፖርት ታደርጋለች።
ፖሊስም ባደረገው ክትትል በ1991 እ.ኤ.አ ሲያገኛት 8+ ዓመቷን ይዛ ነበር።
ፖሊሶች በክትትል ሲያገኟት፣ ከውሾቹ ጋር ስትላፋ፣ ስትጠመጠምባቸው፣ አብረው ሲንከባለሉና ልክ እንደውሾቹም ስትጮኽ ነበር።
ፖሊሶቹ ሲቀርቧት፣ እንደውሻ በቁጣ ጥርሷን እንዳሳየቻቸውና ጥርሶቿም እንደ ውሻ ክራንቻ የሾሉ እንደነበሩ ተናግረዋል።
ስለቤተሰቦቿ ማንነት አጥንተው ከደረሱበት በኃላ፣ የሚገርመው ወደ እርሻ መሬታቸው ካስገቧት፣ ከሰዓታት ግራ መጋባቷ በኃላ፣ እናትና አባቷ ሲመጡና ሊያናግሯት ሲጠጓት በንክሻ መልክ አስፈራርታቸዋለች።
ከዱር ውሾች ተገኝታና ተለይታ ለቤተሰቦቿ ብትሠጥም "They Live Happily Ever After" እንደሚባለው የፍቅር ፊልም ማሳረጊያ ሃረግ ሕይወት አልቀለለቻትም።
ይልቁንስ ወላጆቿ ከነሱ መግባባት ባለመቻሏ፣እንዴት እንደ ሰው መመገብና መጠጣት ባለማወቋና በራሷ ነገሮችን ማድረግ ባለመቻሏ እንደ ሌላ ፍጡርና አንድ አብሯቸው እንደሚኖር የቤት ውሻ ቆጠሯት።
ይኽም ሁኔታ በማሕበረሰቡና በአካባቢው በሚታተሙ ዝነኛ ጋዜጦች ሳይቀር "Dog Girl" የሚባል ስያሜ አሰጣት።
"ትንሿ እንስሳ፣ በአራት እግሯ ምትራመደው፣ እንደውሻ ምትበላው" የሚሉ ስነልቦናዊ አግባብነት የሌላቸው ስያሜዎች ተጨመረላት።
የጤናዋን ሁኔታ ምትከታተልላት ዶክተር በዘገባዋ ላይ Oxana እንድታገግም እንክብካቤ በምታደርግበት ወቅት የገጠማትን አስቸጋሪ ሁኔታ ስትገልጽ "ልክ ውሻ እንደማላመድ ያኽል ነው። የሆነ ትህዛዝ እንድትሰማና የእጆቼን የምልክት እንቅስቃሴ ተከትላ እንድትተገብር ማድረግ ነበረብኝ።" ብላለች።
እንድታወራ በምትለማመድና በምትማርበት ወቅት ከአንደበቷ ምታወጣቸው ቃላት እንግዳና ልዩ የሆኑ ከሙት ሰው የሚወጡ የመሰሉ፣ለዛ፣ቃናና ዜማ የሌላቸው ነበሩ።
ከሷ ድምፅ ይልቅ ሮቦት እንኳን የሚያወጣው ድምፅ ለሰው የቀረበ ነው። የሷ ድምፅና ንግግር እጅግ የሚረብሽ፣ እንስሳት መናገር ቢችሉ እንዲኽ ባለ ለጆሮ በሚቀፍ መልኩ ይሆናል ብለው አስበው እንደማያውቁ" ዶክተሯና አብረው የሰሩ ሰዎች ተናግረዋል።
ባላሳለሰ ጥረትና እንክብካቤ "ወደ ሠውነት" ተሻሽላ ቀስ በቀስ ቃል አውጥታ ዶክተሮቿን እንደ እንስሳ ሳይሆን እንደ ሠው ደርሳ እስክታመሰግን ተለወጠች።
በፊት ምትፈልጋቸውንና የወደደቻቸውን ነገሮች መሬት ቆፍራ ቀብራ ትሸሽጋቸው ነበር። አሁን አልጋዋ ላይ ትራሷ ውስጥ ታስቀምጣቸዋለች።
22 ዓመቷ ቢሆንም የአእምሮዋ ውቅር ልክ የ6 ዓመት ሕፃን ልጅ ያለበት ሁኔታ ላይ ነው።
ቃል መግባት አውቃበታለች አትተገብረውም እንጂ፣ፊደላት ምን እንደሚመስሉ መለየት ጀምራለች መፃፍና ማንበብ አትችልም እንጂ።
አስፈላጊው እንክብካቤ እየተደረገላት በልዩ የልጆች ማቆያ በእግሮቿ እንድትራመድ፣ በአግባቡ እንድታወራ፣ ድርጊቷና ሁኔታዎቿ እንደ ሰው እንዲሆኑ ተለማምዳ በመጨረሻም ተሳክቶላት "አንዲት ወጣት ሴት" በመባል መደበኛ ሕይወቷን ለመኖር በቅታለች።
አሁን ይኽ ፅሁፍ በተፃፈበት ጊዜ ( 2013 ዓ.ም) ዕድሜዋ 35+ ሆኗል። የአእምሮ ውስንነት ያለባቸው ሰዎች ህክምና መስጫ ሆስፒታል ውስጥ በግብርና ሙያ በበላይ አለቆቿ ክትትል እየተደረገላት እያገለገለች ትገኛለች።
#ማጠቃለያ
ከላይ ካነሳነው የጥንቶቹ መንትዩች Remus እና Romulus በተኩላ ማደግ ታሪክ፣
የዚኽችም በዚኽ ዘመን ከሆነው ውሻ ያሳደጋት ሕፃን ታሪክ እና ሌሎችም ይኽንን መሰል ክስቶች፣ ኹሉ ይልቅ የሚገርመውና አስደናቂው ነገር እንስሳት ሕፃናትን እንደራሳቸው ሕፃናትራሳቸው ሕፃናት አይተው ልዩነት ሳይፈጥሩ እያጠቡ ተንከባክበው ማሳደጋቸው ነው።
ቸር ሠንብቱ
(ነጽሩ ወዘሠናየ አጽንዑ)
-
LIVE
Sean Unpaved
2 hours agoSnap Counts & Showdowns: Hunter's Usage, CFB Fire, & Playoff Baseball Bonanza
3,883 watching -
56:09
Steven Crowder
4 hours agoBlack Fatigue is Real and I Told Them Why | Black & White on the Gray Issues
253K1K -
DVR
Simply Bitcoin
2 hours ago $0.33 earnedLEAKED CONVERSATION: US SECRET Bitcoin Plan EXPOSED?! | EP 1350
2621 -
3:36:42
Barry Cunningham
14 hours agoBREAKING NEWS: PRESIDENT TRUMP HOSTS FULL CABINET MEETING!
17.4K8 -
1:59:05
The Charlie Kirk Show
2 hours agoTurning Point Halftime + Antifa Panel Aftermath + Right-Wing Taylor Swift? |Patrick, Cuomo|10.9.2025
31.1K24 -
27:46
Jasmin Laine
3 hours agoCBC TURNS On Carney After Trump HUMILIATES Him–Poilievre’s Response Goes Viral
3045 -
4:27:44
Right Side Broadcasting Network
6 hours agoLIVE REPLAY: President Trump Hosts a Cabinet Meeting - 10/9/25
87.2K44 -
1:13:52
Mark Kaye
2 hours ago🔴 Schumer BUSTED Celebrating Democrat Shutdown!
3.76K4 -
1:00:33
Timcast
3 hours agoTrump To Declare Antifa FOREIGN Terrorist Org, Antifa Leaders FLEE Country
120K95 -
2:41:53
MattMorseTV
4 hours ago $6.53 earned🔴Trump's Cabinet Meeting BOMBSHELL.🔴
40.7K35