ቡሽ (የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝደንት) ለኢራቅ ወረራ ፑቲንን አውግዘዋል || Bush condemns Putin's invasion of 'Iraq'

1 year ago
1

ቡሽ (የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝደንት) ለኢራቅ ወረራ ፑቲንን አውግዘዋል።

ቡሽ በንግግራቸው ፑቲን 'ኢራቅ'ን መውረሩን አምርረው አውግዘዋል (ንግግራቸው ዩክሬንን በተመለከተ ቢሆንም ትልቅ ስህተት ፈጽመዋል)

የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆርጅ ደብሊው ቡሽ በአጋጣሚ የቭላድሚር ፑቲንን "ኢራቅ" ወረራ አውግዘዋል፣ ነገር ግን ወድያው "ስለ ዩክሬን እያወራሁ ነው" ሲሉ እራሳቸውን ለማስተካከል ሞክረዋል ።

ሚስተር ቡሽ ይህን የገለፁት በዳላስ ቴክሳስ በተደረገ አንድ ዝግጅት ላይ ስለ ፍትሃዊ ምርጫ አስፈላጊነት ንግግር ባደረጉበት ወቅት ነው።

እሱም "አንድ ሰው ኢራቅ ላይ ሙሉ በሙሉ ፍትሃዊ ያልሆነ እና አረመኔያዊ ወረራ ለመጀመር የወሰነው ውሳኔ ... እኔ ዩክሬን ማለቴ ነው" ብለዋል።

እ.ኤ.አ. በ 2003 በአሜሪካ መሪነት ኢራቅን በወረረችበት ወቅት ሚስተር ቡሽ ፕሬዝዳንት ነበሩ።

#Bush_condemns_Putin's_invasion_of_Iraq_Instea_of_Ukraine

Loading comments...