ከሰማይ የወረደው መና ኢትዮጵያ ውስጥ❗መና ማምረቻ ማሽን ሰርቻለኹ❗ ሳይንስ 🔬 መና ይመገብ የነበረው ቅዱስ ኢትዮጵያዊ ንጉሥ Manna part - 2 |

2 years ago
15

#መጽሐፍ_ቅዱስ ቅዱስ_ቁርዓን
What did Israel eat in the wilderness?
christian religion
bible wisdom
christian story
old testament
bible exodus
exodus 16
manna bible
quail bible
moses exodus
Manna
What is manna?
manna meaning
manna from heaven meaning
ሙዳዬ መና
EOTC
#Manna
#What_is_manna?
#What_did_Israel_eat_in_the_wilderness?
What is it?
#Exodus
Wilderness journey
Wilderness of Sin
Marah
Elim
by the Red Sea
Canaan
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉 የመና አስገራሚ ተፈጥሮ
የእስራኤል ልጆች ለዕለት የሚበቃቸውን እንዲለቅሙ ቢነገራቸውም ስላልሰሙ እንዲኽ ሆነባቸው....
ዘፀሐት ምሕራፍ 16 ከቁጥር  ፲፯-፲፰ "...አንዱ አብዝቶ አንዱ አሳንሶ ለቀመ።እጅግ ለለቀመ አልተረፈውም። ጥቂትም ለለቀመ አልጎደለበትም።"
ለነገ እንዳያስቀሩም ቢነገራቸው አልሰሙም እና ዘፀሐት ምሕራፍ 16 ቁጥር 20 ላይ የሆነባቸውን እንዲኽ ይነግረናል  "ነገር፡ግን፥ሙሴን፡አልሰሙትም፤አንዳንድ፡ሰዎችም፡ከርሱ፡ለነገ፡አስቀሩ፥ርሱም፡ተላ፡ሸተተም፤ሙሴም፡ ተቈጣቸው።"
የመና አለቃቀም ማታና ጠዋት ሆኖ ጠሉ እስኪጠፋ ድረስ የሚበቃቸውን ያኽል ከለቀሙ በኃላ እንዲህ ይሆናል... ዘፀ ምሕራፍ 16 ቁጥር 21 "ሰውም፡ዅሉ፡ዕለት፡ዕለት፡የሚበላውን፡ያኽል፡በጧት፡ለቀመ፤ፀሓይም፡በተኰሰ፡ጊዜ፡ቀለጠ።" ይለናል።
ይኽን የተፃፈ መረጃ ይዘንም "ይኽ "መና" የተባለ ነገር ፣ ከአንድ ቀን በላይ አያድርም ቶሎም ይበላሻል" ብለን እንዳንደመድም ደግሞ ሙሴ ቀጣዩ ሰንበት ወይም ቅዳሜ በመሆኑ በስድስተኛው ማለትም ዕለተ አርብ ቀን ለቅመው እንዲያበቁና የለቀሙትን  እንዲያሳድሩ ነገራቸው ይለናል...
ዘፀ ምሕራፍ 16 ቁጥር 24 "ሙሴ እንዳዘዘ ለነገ አኖሩት አልሸተተም ትልም አልሆነም።" ይለናል።
ለቀናት ማደር እና መዋል ብቻ አይደለም ይባስ ብሎም ይኽ አስገራሚ ህብስተ-መና
እግዚአብሔር ለሙሴ ባዘዘው መሰረት በዚያን ጊዜ ከ2000 ዓመታት በፊት ከሰማይ የወረደውን መና ለምስክርነት ይሆን ዘንድ ለልጅ ልጅ እንዲቀመጥ ማድረጉን ደግሞ ስንሰማ የበለጠ ይገርመናል።
ዘፀሐት ምህራፍ 16 ቁጥር 33 ላይ " ሙሴም፡አሮንን፦አንድ፡ማድጋ፡ወስደኽ፡ጎሞር፡ሙሉ፡መና፟፡አግባበት፥ለልጅ፡ልጃችኹም፡ይጠበቅ፡ዘንድ፡ በእግዚአብሔር፡ፊት፡አኑረው፡አለው።" ይለናል ቅዱስ መጽሐፍ
ለክፍለ ዘመናት ፣ እስካሁንም ሳይበላሽ ቆይቷል / ወደፊትም ይቆያል ማለት ነው።
¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶
አንዳንድ ስለ መና እርስ በርሳቸው የሚጋጩ የሚመስሉ ገለጻዎች ከተለያዩ ንግርቶች ፣ ወጎች እና ጥንታዊ ባህሎች የወጡ ሲሆን :-
የባቢሎናዊው ታልሙድ እንደሚያስረዳው " ይኽ የመና ገለጻ ልዩነት የመጣው መናውን ማን እንደበላው በመለየት ፣ የጣዕሙ ወይም የገለጻው ልዩነት እንዴት እንደተፈጠረ " ያብራራልናል ፣
ለምሣሌ :-
👉 መና ለትናንሽ ሕፃናት እንደ ማር ይጣፍጣል፣
👉 ለወጣቶች እንደ እንጀራ /ዳቦ ያለ ጣህም ሲኖረው ፣
👉 አረጋውያን ሲቀምሱት የዘይት ጣዕም  እንደሆነ ገልጿል።

በተመሴይም ፣ ክላሲካል ረቢኒካዊ ሥነ-ጽሑፍ "መና ከጤዛ በፊት ወይስ ከጤዛ በኋላ መጣ ?" የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ ይሞክራል ፣
ይኽውም "መና በሁለት ጠል መካከል የሚመጣ መሆኑን በመግለጽ
አንዱ ከመና በፊት ወድቆ ሌላኛው ደግሞ በኋላ ወድቆ የሚገኝ ነው " ይለናል።
በሌሎችም ስነ-ጹዑፋዊ ገለጻዎች እንዲኹ አስገራሚ ትርክቶች አሉት።
እንደ ተፈጥሯዊ የምግብ ንጥረ ነገር መና ተረፈ ምርቶችን ያመርታል ፣
ነገር ግን በጥንታዊ ረቢኒካዊ ሥነ-ጽሑፍ ውስጥ ፣ ከተፈጥሮ በላይ የሆነ ንጥረ ነገር እንደሆነ እና ፣ መና ምንም ብክነት እንደሌለው እና ተረፈ-ነገር እንደማያመጣም ይነገር ነበር፣

በዚህም ምክንያት ከበርካታ አሥርተ ዓመታት በኋላ ፣ መና ከሰማይ መውረድ ካቆመ በኋላ እንኳን በእስራኤላውያን መካከል " መጸዳዳት እንዳልቻሉ እና እንደተቸገሩ" ይታመን ነበር።

እንደሚታወቀው ዘመናዊው የሕክምና ሳይንስ እንዲህ ዓይነቱን ረጅም ጊዜ መጸዳዳት ያለመቻል ከፍተኛ የአንጀት ችግርን ያስከትላል ፣  "በተለይም ከመና በኃላ ሌሎች ምግቦች እንደገና ጥቅም ላይ መዋል ሲጀምሩ ይኽ ችግር እየጎላ መጣ" ይላሉ።

በዚኽ ጉዳይ ላይ የፃፉ የጥንታዊ ረቢ ጸሃፊዎች እስራኤላውያን ያጉረመረሙት መጸዳዳት አለመቻላቸው እና የአንጀት ችግር ያሳስባቸው እንደነበር ይናገራሉ።

ብዙ የክርስቲያን ቬጀቴሪያኖች ወይም አተክልት ተመጋቢዎች " አምላክ በመጀመሪያ ሰው ሥጋ እንዳይበላ አስቦ ነበር " ይላሉ ፣ ምክንያቱም ዕፅዋት መንቀሳቀስ ስለማይችሉ መግደል ኃጢአት አይሆንም፡
በዚኽም "ሥጋ ያልሆነ ነገር" የሆነው መና ይህንን ጽንሰ ሐሳብ ለመደገፍ ይጠቅማል።

በተጨማሪም፣ ሰዎቹ ሲያጉረመርሙና ሥጋን ሲመኙ፣ እግዚአብሔር ድርጭትን ሰጣቸው፣ ነገር ግን እነሱ አሁንም አጉረመረሙ እና አንዳንዶችም በመና ምትክ የተላከላቸውን ድርጭቶች በስስት ሰበሰቡ ።

"የድርጭትን ሥጋ ገና በጥርሳቸው መካከል ሳለ፥ ሳይታኘክ፥ የእግዚአብሔር ቍጣ በሕዝቡ ላይ እንደደ።" መጽሐፍ ነግሮናል ፣ ይኽንንም በቀደመ ክፍል አይተናል ።

👉 ሌላው አስገራሚ ጉዳይ የመና ጥቅም ለምግብነት ብቻ አልነበረም ፣ አንድ የጥንታዊ ረቢ ምንጭ እንደገለጸው "ጥሩ መዓዛ ያለው የመና ሽታ ለእስራኤላውያን ሽቶ ይሠራበት እንደነበር " ይገልጻል።

ታልሙድ እንደሚለው፣ መና በአምላክ ላይ ጠንካራ እምነት ካላቸው ሰዎች ቤት አጠገብ እና ጥርጣሬ ካላቸው ሰዎች ቤት ርቆ ተገኝቷል።

መና በጉዞ ላይ ካሉት ከእስራኤላውያን ሌላ አህዛዝስ ቀምሰውት እንደሆነ ስንጠይቅ የምናገኘው ምላሽ ፣

በእርግጥም አንድ ጥንታዊ ሚድራሽ መጽሐፍ "መና በእጃቸው ስለሚንሸራተት ለአህዛብ የማይዳሰስ ነበር" ይለንና

ሚድራሽ የተባለው ጥንታዊ መጽሐፍ አክሎም " መና እንደቀለጠ ፣ ፈሳሽ ጅረቶችን እንደፈጠረ፣  እነዚኽ የቀለጠ መና የተቀላቀለባቸው ጅረቶች በእንስሳት እንደተጠጡ ፣ የእንስሳቱንም ስጋ መና እንደተዋሃደው በዚህም በተዘዋዋሪ መና በአህዛብ መበላቱን ይናገራል፣ ይህም አሕዛብ መና የሚቀምሱበት ብቸኛው መንገድ" እንደሆነ ይነግረናል።

እነዚህ ያልተመጣጠነ ስርጭት እና ገለጻ ያላቸው ጥንታዊ ሰነ-ጹሑፋዊ ምንጮች በአማካይ ተመሳሳይ ፍንጭ ያላቸው ሲሆኑ ጽሑፎቹ "መና በየቀኑ በከፍተኛ መጠን ይወርዳል" የሚለውን አመለካከት ኹሉም በተመሳሳይ ይጋራሉ።

  መና እስከ 2,000 ክንድ ስፋት ያኽል ሜዳ ላይ ተዘርግቶ ፣ ከ 50 እስከ 60 ክንድ ቁመት ያለው፣ እስራኤላውያንን ለ 2,000 ዓመታት ለመመገብ በቂ እና በምስራቅ እና በምዕራብ ላሉት ነገሥታት ሁሉ ከቤተ-መንግስታቶቻቸው እንዲታይ መደረጉ ፣ ይነገራል።

¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶

👉 " የመና ናሙና ኢትዮጵያ ውስጥ ይገኝ ይሆን? " ብለን የጠየቅን እንደሆነ

ከቅዱስ መጽሐፍ የሚከተለውን ፍንጭ እናገኛለን 👇

ከላይ  ዘፀሐት ምህራፍ 16 ቁጥር 33 ላይ እንዳየነው " ሙሴም፡አሮንን፦አንድ፡ማድጋ፡ወስደኽ፡ጎሞር፡ሙሉ፡መና፟፡አግባበት፥ለልጅ፡ልጃችኹም፡ይጠበቅ፡ዘንድ፡ በእግዚአብሔር፡ፊት፡አኑረው፡አለው።" ብሎናል ቅዱስ መጽሐፍ

ለናሙና ለልጅ ልጅ የተቀመጠ መና እንዳለ መጽሐፍ ከነገረን ፣ ታድያ ይኽ ለናሙና የተቀመጠው መና ኢትዮጵያ ውስጥ ይሆን ብለን መጠየቃችን አንድምታው ምን ይሆን? ብለን እንጠይቅ ምክንያቱም

መጽሐፍ ቅዱስ የመናውን ናሙና በምሥክሩ ታቦት ውስጥ እንዳስቀመጡት በግልጽ ስለነገረን መረዳት እንችላለን።

ዘፀሐት ምሕራፍ 16 ቁጥር 34 "...እግዚአብሔርም፡ሙሴን፡እንዳዘዘው፡እንዲሁ፡ይጠበቅ፡ዘንድ፡አሮን፡በምስክሩ፡ፊት፡አኖረው።" ይላልና

በሚገርም ኹኔታ "መና በምስክር ታቦቱ የመቀመጡን ሃቅ" እውነት የሚያስብለው ብሉይን አልፈን አዲስ ኪዳን መጽሐፍትን ስናገላብጥ ስለ መና ተጽፎ ተጠቅሶ እናገኛለን ፣

ጳውሎስ ወደ ዕብራውያን ሰዎች በፃፈው መልዕክት ላይ ስለ ታቦቱ በ ዕብራውያን ምህራፍ ፱ ቁጥር ፬ ላይ እንዲህ ይላል...

"በዚያም ውስጥ የወርቅ ማዕጠንት ነበረ።ዅለንተናዋንም በወርቅ የተለበጠች የኪዳን ታቦት በርሷም ውስጥ መና ያለባት የወርቅ መሶብና የበቀለች የአሮን በትር የኪዳኑም ጽላት ነበሩ።" ተብሎ ተጽፏልና

ይኽንን ጉዳይ በአጭሩ ለመፍታት ስንሞክር ፣ የምስክሩ ታቦት መገኛው ኢትዮጵያ እንደሆነ ይታወቃል።

የታቦቱ መገኛ ኢትዮጵያ መሆኗን ካልካድን በስተቀር ታቦቱ ስር መናው በገንቦ ለትውልድ ምስክርነት መቀመጡን መጽሐፍ ነግሮናል።

ስለዚኽ በምስክሩ ታቦት ስር የተቀመጠው የመና ናሙና ከታቦቱ እና ሌሎች ቅዱስ እቃዎች ጋር ኢትዮጵያ ውስጥ ፣ እርሱ በሚያውቀው ሥፍራ ይገኛል ማለት ነው።

¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶

Loading comments...