ሠላዩ | Double Agent | ባሻ አውዓሎም ሐረጒት part - 2

2 years ago
2

በ1825 ትግራይ አድዋ (እንትጮ ትኩዝ መኸረም) ተወለዱ። በዚህ አካባቢ ሰፊ የእርሻ መሬትና ብዙ እንስሳት ስላላቸው "ሐብታም" ከሚባሉት ነዋሪዎች አንዱ ናቸው።

ለንግድ ሥራ በአፄ ዮሃንስ ዘመን ወደ ሃማሴን ሄዱ::

ራስ አሉላ ጣልያኖች በሰፈሩበት አካባቢ ያለውን እንቅስቃሴ ለመረዳት በፈለጉ ግዜ አውአሎምን መልምለው ለሥለላ ሥራ ላኳቸው::

አውአሎም ሰው ተግባቢ  በመሆናቸው በአጭር ግዜ ውስጥ በጣልያኖች ተቀባይነትን አገኙ።

፩፪፫፬፭፮፯፰፱፲

የአፄ ዮሃንስ ዘመን አብቅቶ አፄ ምኒልክ በተተኩ ግዜ አውአሎም ኑሯቸውን ከጣልያኖች ጋር አድርገው የአድዋ ጦርነት ከመጀመሩ በፊት በህቡዕ ለጣልያኖች የሥለላ ስራ ይሠሩና በየአካባቢው እየተዘዋወሩ በሚስጥራዊ ስለላ መረጃዎችን ለጥልያን መንግስት ያቀርቡ ነበር።

በኃላ አፋቸውን ወደ ጥልያን ልባቸውን ወደ ሃገራቸው ኢትዮጵያ አገልግሎታቸውንም ለሃገራቸው ጥቅም ለማዋል ወሰኑ

እንዴት?? እና ለምን?? የሚለውን እንመልከት

ለመሆኑ ባሻ አውአሎም በታሪክ ስማቸው የሚነሳበት Double Agent ወይም ድርብ ወኪልነት ምንድነው?

ይኽ እጅግ አደገኛ የሆነ የሥለላ ተግባር እጅግ የሥለላ ጥበብ እና ልምድ ባላቸው ሰዎች የሚተገበር ፣ልዩ ክዕሎት ፣የማስመሰል ችሎታ የሚጠይቅ ነብስን ቁማር የማስያዝ አይነት ያለ ተግባር ነው፣

ብዙ ጊዜ በታሪክ እንደምንሰማው  በራሽያ እና በአሜሪካ እና በአውሮፓውያን ሰላዮች የሚተገበር እንደሆነ እና በፊልሞቻቸውም ይኽንኑ አደገኛ ተግባር አሳይተውናል ፣ 
ይኽም ጠላትን ወክሎ ለአንድ ሀገር ወይም ድርጅት ሰላይ ሆኖ የሚሰራ ወኪል ሲሆን ከሁለቱም ወገን የሚታወቀው ለአንዱ እንደሚሰራ እንጂ ለሁለቱም እንዳልሆነ ነው።

ይኽንን አደገኛ ድርጊት አውሃሎም አረጒት ተግብረውታል ፣ ምናልባትም ፊልም ቢሆን አስብሎ የሚያስመኝ ድንቅ ታሪክ እነሆ❗

፩፪፫፬፭፮፯፰፱፲

የአድዋ ጦርነት ከመደረጉ በፊት "ኢትዮጵያና ጥልያን ልዮነታቸውን በእርቀ-ሰላም ሊፈቱ ነው" ይባል ነበር።

የጥልያን የስለላ ክፍል ኃላፊም ይህን ሃሳብ በመቃወም አውአሎም ፊት "የጥልያን መንግስት ኢትዮጵያን ደምስሶ ግዛቷን በቁጥጥር ስር ማዋል አቅቶት ነው እርቅ እርቅ የሚለው?...እንደ ዝንብ እንፈጃቸዋለን"
ሲል ደነፋ::

አውአሎምም ይኽንን በሰሙ ጊዜ ንቀቱ እጅግ አስቆጥቷቸው ስለጉዳዩ ከራስ መንገሻ ዮሃንስ ጋር ተወያዩ ራስ መገሻም ከአፄ ምንይልክና ከእቴጌ ጣይቱ ዘንድ አውአሎምን አቀረቧቸው።

የሃገር ወዳድነታቸውን ምንይልክ ከመረመሩ በኃላ የጣልያንን ጀነራሎች እቅድ የሚያሳክር ብልሃት አብረው ነደፉ።

ለባራቲየሪ በአውአሎም በኩል እንዲነገረው የተፈለገው መረጃም

፨ "የካቲት 21 አርብ ማርያም ነች የሸዋ ሰው ማርያምን ስለሚያከብር ሠራዊቱ ሁሉ አድዋን ለቆ ይወጣል...ቅዳሜን ውሎ አድሮም በቀጣዩ ቀን እሁድ የካቲት 23 ቀን የሰንበት ጊዮርጊስን ለማክበር ቤተ ክርስቲያን ይሄዳል። ምንይልክና ጣይቱ ከጥቂት ዘበኞች ጋር ስለሚገኙ ባራቲየሪ ድንገተኛ ወረራ ቢያደርግ እነሱን መማረክ ይችላል" የሚል ነበር በአዋሎም በኩል ለጥልያኖች ሊተላለፍ የተፈለገው አሳካሪ መልዕክት።

እቴጌ ጣይቱ አውአሎም ከመሄዱ በፊት አስጠርተው ምግብና መጠጥ አቀረቡላቸው "ይህ ምግብና መጠጥ እንደ ሥጋ ወደሙ ቆጥረህ አገርህን ላትከዳ ምለህ ብላ" አሏቸው አውአሎምም የተባሉትን አድርገው ግዳጃችውን ለመፈፀም ተጓዙ።

፩፪፫፬፭፮፯፰፱፲

ባራቲየሪም የተነገረውን አመነ። የካቲት 23 እማርካቸዋለሁ በሚል የካቲት 22 ሰራዊቱን ወደ ኢትዮጵያ ይዞታ አስጠጋ። በጦር ሜዳ መነፅርም ሲመለከት እነ እምዬ ድንኳናቸውን ሆነ ብለው አንስተውት ስለነበር በድጋሚ አመነ!::

የካቲት 23 ጠዋት የእርችት ተኩስ አሰማ የአድዋ ጦርነት ተጀመረ...የምንይልክ ሠራዊትም ካደፈጠበት ወጣ።

አውአሎምና ጓደኛው ከጣልያን ተለይተው ወደ ወገኖቻቸው ኢትዮጵያውያን ሲቀላቀሉ የተመለከተው የጣልያን መኮንን  "አውአሎም! አውአሎም!" እያለ ሲጣራ

አውአሎም "ዘወአል ካዩ እያወዕለኒ" ብሎ አፌዘበት "የዋልከውን አያውለኝ" እንደማለት ነው።

፩፪፫፬፭፮፯፰፱፲

ምንይልክ ከድሉ በኃላ የአውአሎምን ውለታ ሳይዘነጉ የ"ባሻ"ነት

ማህረግና ሽልማቶችን ሰጧቸው። ባሻ አውአሎም ሐረጒት እድሜና ዘር ታድለው በተሰጣቸው ርስተ-ጉልት በደስታ ኖረው በእርጅና ሞቱ።

ጥልያን ድጋሚ ከ40 ዓመት በኃላ ኢትዮጵያን ሲወር ባሻ አውአሎም የአንድ ሰራዊት ያህል እንደጒዱት ያውቃልና የአርባ አመት ቂሙን የባሻ አውአሎም ልጅ፤የልጅ ልጅና ወገን የሆነን ዘር ሁሉ እያስለቀመ ፈጅቶታል::

እኔ ደግሞ ለሃገሪትነ ኢትዮጵያ ውለታ የዋሉትን ሁሉ እያመሰገንኩ እጅ  አነሳቸዋለሁ::

Loading comments...