ኤርትራ ከሩስያ የተረከበቻቸው || አጥፍቶ ጠፊ ድሮኖች Ethiopia Russia Eritrea

1 year ago
2

Zala KYB ድሮኖች

(ቱካ ማቲዎስ)

እነዚኽ ዛላ ኬዋቢ የተሰኙ አደገኛ ድሮኖች የሩቅ መሬት እና የባህር ኢላማዎችን በትክክል ለመምታት በሩሲያ ጦር ምህንድስና የተገነቡ ካሚካዝ ወይም አጥፍቶ ጠፊ ድሮኖች ናቸው።

እነዚኽ ድሮኖች አንድ የተወሰነ ዒላማ ብቻ ለመምታት ነው አገልግሎት ላይ የሚውሉት።

ይህ ድሮን ለአንድ ጊዜ ጥቃት ብቻ የምንጠቀምበት ሲሆን ፣ አጥፍቶ ጠፊ በሚል ቅጥል ስምም ይታወቃል፣

ኢላማውን ለመምታት የድሮኑ ሙሉ አካል ጭምር ነው እንደ ማጥቂያነት የሚውለው በዚኽም ጃፓን በኹለተኛው የሃለም ጦርነት ለአጥፍቶ ጠፊ ተዋጊ ጄቶቿ በሰጠችው ስያኔ ካሚካዝ በሚል ተሰይመዋል።

ጭነታቸው እስከ 3 ኪሎግራም የሚመዝኑትን እነዚኽን ሰው አልባ ድሮኖች የሩስያ ጦር በዩክሬን ባደረገው ወታደራዊ ዘመቻ ከፈንጂ ጋር መጠቀሙ ተዘግቧል።

ዛላ ኬዋይቢ በመሬት እና በባህር ላይ አነስተኛ መጠን ያላቸውን ኢላማዎች ውጤታማ በሆነ መንገድ ለማጥፋት የሚያስችል ስርዓት የተገጠመለት ድሮን ነው።
#Ukraine
እነዚኽ የድሮን ሥሪቶች ልክ ለጥፋት እንደ የተመራ መንጋ ወይንም ግሪሳ ወፍ አይነት ሆነው ሊሠሩ እና በብዛት ሆነው አንድ ትልቅ ኢላማ ላይ መጠነ ሰፊ ውድመት ሊያደርሱ ይችላሉ።

ሰው አልባ አውሮፕላኑ ከራሱ ማስወንጨፊያ ወይም ከባህር ኃይል መርከብ ላይ ሊነሳ ይችላል።

ዛላ KYB-UAV፣ እንዲሁም #KUB_BLA (Cube) በመባል የሚታወቀው፣ በካላሽኒኮቭ ግሩፕ ቅርንጫፍ በሆነው ዛላ ኤሮ በሩሲያ መከላከያ ኩባንያ ተሠርቶ የተሠራ አዲስ የድሮን ሥርዓት ነው።

ይኽም የድሮን ግንባታ ስሪት እ.ኤ.አ. በ 2015 እና 2018 መካከል በሶሪያ ውስጥ በሩሲያ የጦር ኃይሎች ባደረጉት የውጊያ ልምድ ላይ የተመሠረተ ነው ።

እውቅና ያገኘውም በአቡዳቢ በተካሄደው የአለም አቀፍ የመከላከያ ኤግዚቢሽን እኤአ በ2019 ለመጀመሪያ ጊዜ በሩስያ ጦር ለእይታ ቀርቦ ነው።

ለወታደራዊ ኢላም ብቻ የሚውለው ይኽ ሰው አልባ በራሪ የተሰጡትን ወይም የተቀመጡለትን የዒላማ መገኛዎች ወይም በምስል ላይ ያሉ የዒላማ መመሪያ በመመስረት ለወታደራዊ ጥቃቶች የሚሆኑ የተለያዩ አነስተኛ መጠን ያላቸውን የጦር መሳሪያዎች ጭነትን በአስገራሚ ትክክለኛነት ያቀርባል።

ከዚኽ አገልግሎት በተጨማሪ በመሬት ላይ እና በባህር ላይ ትናንሽ መጠን ያላቸውን ኢላማዎች ውጤታማ በሆነ መንገድ ለማጥፋት እንደ ራሱን አጥፊ ሰው አልባ አውሮፕላን ወይም ካሚካዜ አውሮፕላን መጠቀም ይቻላል።

ዩክሬናውያን በሰሞኑ ሩሲያ የዩክሬን ጦርነት በኪየቭ አውራጃ በፖዲልስኪ ውስጥ ፈንጂ የተገጠመለትን የዛላ ኬዋይቢ ሰው አልባ አውሮፕላንን መትተው መጣላቸውን ተናግረዋል

Zala KYB ሰው አልባ አልባሳት ንድፍ እና ባህሪያት

ሰፊው ባለሶስት ማዕዘን ክንፍ ያለው ሰው አልባ አየር ተሽከርካሪ #unmanned_aerial_vehicle  #UAV በተልእኮዎች ወቅት በድምጽ አልባ ማስወንጨፊያዎች እና ተልህኮውንም በፀጥታ እንዲሠራ ተደርጎ የተሰራ ነው።

በዚኽም ስሪቱ በመሬት እና በባህር ላይ የተመሰረተ የጠላት መሠረተ ልማትን እንዲሁም ቀላል የታጠቁ ኢላማዎችን ማጥቃት ይችላል።

ይኽ ሰው አልባ አውሮፕላን ክንፉ 1.21ሜ ፣ ርዝመቱ 0.95 ሜትር እና ቁመቱ 0.165 ሜትር ርዝመት አለው።

እንደ ቅኝት፣ ስለላ  እንዲሁም ዒላማን ለይቶ መጠቆም ላሉ ተልእኮዎች ሊያገለግል ይችላል።

የዛላ #KYB_UAV አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ቪዥዋል መለያ ቴክኖሎጂን ለእውነተኛ ጊዜ እውቅና እና ዒላማዎችን መመደብ ያካትታል።

የ AIVI ቴክኖሎጂ በአንድ በረራ ወቅት የተሸፈነውን ቦታ በ 60 ጊዜ ያሳድጋል እና የድሮንን የእውነተኛ ጊዜ ገዳይነት እና ራስን በራስ የማስተዳደርን ያሻሽላል።

የድሮኑ አፈፃፀም ምን ይመስላል?

የድሮኑ የጅራቱ ክፍል ወንጨፊያን ሲያካትት ፣  በኤሌክትሪክ ሞተር አሃድ የሚንቀሳቀሰው ሰው አልባ አውሮፕላኑ በሰአት ከ80 ኪሎ ሜትር እስከ 130 ኪ.ሜ ይጓዛል።

የሆድ እቃው ከፍተኛው እስከ 3 ኪሎ ግራም ሴንሰሮችን እና ፈንጂዎችን የመሸከም አቅም አለው።

በአየር ላይ ለ 30 ደቂቃዎች ሊቆይ እና በግምት እስከ 40 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ኢላማዎችን ይመታል።

ሩስያ በአብዛኛው ይኽን ዛላ ኬዋይቢ #Zala_KYB ድሮን የምትጠቀመው ለውትድርና እና ስለላ አገልግሎት ነው። 

ለኤርትራ የተሰጣት ድሮን በቁጥር ስምንት እንደሆና ተዘግቧል ይኽ ማለት በነዚኽ ስምንት ድሮኖች የተመረጡ ስምንት ኢላማዎችን ብቻ ኤርትራ ትመታለች ማለት ነው ፣ ተጨማሪ ዘጠነኛ ኢላማ ኤርትራ ለመምታት ብትፈልግ ሌላ ድሮን ያስፈልጋታል ማለት ነው።

Loading comments...