የኔ ምርጫ ግራጫ || እጅግ አስደናቂው ቀለም

1 year ago
4

የኔ ምርጫ ፣ ግራጫ!
የ ግራጫ #Gray ቀለም አስደናቂ ምንነት?

(ቱካ ማቲዎስ)

ግራጫ ማለት ምን ማለት እንደሆነ እንዴት እናውቃለን? ትናንሽ የጫካ ወፎችን ከጥቃት ሰውሮ የሚደብቀው ግራጫ ቀለም ፣ ግራጫ ከኢንዱስትሪያዊ ማስጌጫዎች ውስጥ ፈዛዛው ነው ፣ተመራጭ ነው? ወይስ ለቀለምነት የማይገባ ገለልተኛ ነው? ግራጫ ሱፍ መልበስ ውስብስብነት ነው ወይስ ማራኪ? ጥርት ያለ ነጭም ሆነ አስገዳጅ ጥቁር፣ ግራጫ የመጨረሻው ተደራዳሪ ነው።

#በቀለም_ሳይኮሎጂ ፣ ግራጫው ገለልተኝነትን እና ሚዛናዊነትን ይወክላል። የቀለሙ ትርጓሜ የሚመጣው በነጭ እና በጥቁር መካከል ያለ ከመሆኑ የተነሳ ነው።
ነገር ግን፣ ግራጫ አንዳንድ አሉታዊ ፍችዎችን ይይዛል፣ በተለይም ወደ ድብርት እና ፍዛዜ የሚያደላ ነው ስለሚባል።

ቀለም አልባነቱ ግራጫን አሰልቺ ያደርገዋል ፣ ግራጫ ለቅርጸ-ቁምፊ (Font color) ቀለም፣ ለራስጌዎች (Headers) ፣ ለግራፊክስ እና እንዲያውም ግራጫ ቀለም አንድ ምርት ብዙ ተመልካቾችን እንዲማርክ ሊያገለግል ፣ ጥቅም ላይ ሊውልም ይችላል።

አፕል በብራንድነታቸው ውስጥ ግራጫ ቀለምን ለሚጠቀሙ ምርቶች ስም ምሳሌ ነው።
ከሁሉም በላይ ብዙዎቹ ላፕቶፖቻቸው በግራጫ ወይም ብርማ ቀለም ቃና ውስጥ ናቸው።

ምክንያቱም ገለልተኛ ቀለም ማንንም አያሸሽም።
በድረ-ገጻቸው ላይ ከነጭ አርማ ጋር ለማጣጣም ግራጫውን ቀለም ለራስጌ (Headers) ይጠቀማሉ።
ነገር ግን፣ በምልክታቸው (በብራንዳቸው) ኹል ጊዜ  በነጭ፣ ጥቁር እና ግራጫ መካከል ያለውን ሚዛን ያሳያሉ ይህም ንፁህ እና ገለልተኛ #Neutral ገጽታን ለመጠበቅ ይረዳል።

ከሥነ ምግባር አኳያ ግራጫ ቀለም አሻሚ ያልሆነ እና የማያዳላ ነው ፣ ግራጫ የውስብስብነት ቀለም ነው–በፍጽምና መካከል የሚወድቀው ቀለም ነው።
ግራጫ ቀለም ታይቶ በቀላሉ ሊታለፍ ይችላል ፣ ነገር ግን ትንሽ ጠለቅ ብለው ካዩት በጣም አስደናቂ ቀለም ነው።

የግራጫ ቀለም አካላዊ ተፅእኖዎች

የግራጫ አካላዊ ተፅእኖዎች ከሌሎቹ ቀለሞች ያነሱ ናቸው። ነገር ግን በሌሎች ቀለሞች እና በስሜታችን ላይ የማቀዝቀዝ ተጽእኖ ይኖረዋል ።

ግራጫ የተረጋጋ እና ግኑን ስሜት የማይሰጥ ነው ፣ ግን በጣም ብዙ ግራጫ ፣ በተለይም ጥቁር ግራጫ ከሆነ - ድባቴ ስሜት የሚሰጥ ሊሆን ይችላል።

ግራጫ ፍጹም ገለልተኛ ነው ። ምክንያቱም ደማቅ ቀለሞችን ማመጠጠን እና የቀለማትን መርሃ ግብር መሳብ ማመጣጠን ይችላል።

የግራጫ ምልክት እና ትርጉም

ግራጫ የማሰብ/ሃሳባዊነት እና የመስማማት ቀለም ነው። በጥቁር እና በነጭ መካከል ያለውን ርቀት ሁሉ በማደራደሩ በማጣጣሙ ዲፕሎማቲክ ቀለም ነው።

እኛ በተለምዶ ግራጫውን ወግ አጥባቂ፣ የሚያምር እና አሪፍ ነው ብለን እንቆጥራለን፣ ምንም እንኳን ትንሽ ሚስጥራዊ ቢሆንም።

ግራጫ የእውቀት ፣ የጥበብ እና የብልህነት ቀለም ነው። ቀለሙ ክላሲክ፣ የጠራ፣ የተከበረ እና ወግ አጥባቂ እንደሆነ ይታሰባል፣ ግራጫ በጥቁር እና ነጭ ጽንፎች መካከል የሚኖር ፍጹም ገለልተኛ ነው።

ቀለሙ ከአዎንታዊነት ያለው ተዛምዶ

ግራጫን እንደ ጥብቅ እና ከባድ ወግ አጥባቂ ፣ የሥራ ሱፍ ልብሶች እና ውስብስብነት ቀለምነቱ ብዙ ጊዜ ይታሰባል።

ግራጫ የጽንፍ ቀለም አይደለም ፣ መካከለኛው ቦታ ያለ ቀለም ነው ምክንያታዊ ስምምነትን የሚያሳይ።
ግራጫ ከጥበብ ከብልህነት ጋርም ይያያዛል - በእድሜ የተገኘ ብስለትን የሚወክል እና ከግራጫ ፀጉር ጋር አብሮ የሚሄድ አይነት።

የግራጫ ቀለም ጠቅላላ ትርጉም - የተጣራ ፣ የተከበረ ፣ ወግ አጥባቂ ፣ ዝቅ ያለ ፣ የሚያምር እና ስልጣን ያለው ነው።

የግራጫ አሉታዊነት

ግራጫ ከስሜት የራቀ ወይም የተቋረጠ እንደሆነ ሊታሰብ ይችላል፣ እና ከሥነ ምግባር አጠያያቂ ጉዳዮች ጋርም የተያያዘ ነው።

አንድም ሆነ ሌላ አይደለም–እንደ እንግሊዝኛ ዘይቤያዊ አነጋገር ወላዋይነትን ለመግለጽ "gray area,"  ወይም “ግራጫ አካባቢ”  እንደሚሉት ቆራጥ እንዳልሆነ ልናስበው እንችላለን።

ግራጫን ከጥበብ ጋር ብናገናኘውም፣ ግራጫ ፀጉርን ለማቅለም በየአመቱ በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር ለጸጉር የሚወጣው ስንመለከት ግራጫን እንደማንወደው ያሳያል።

ግራጫ

"ግራጫ" ተብሎ የሚጠራው ክሪዮላ ክሬዮን የቀለም አይነት በ1934 ተጀምሮ እውቅና አገኘ ። ሌሎች የግራጫ አይነቶች ደግሞ፡- ግራጫ ሰማያዊ፣ ዶልፊን ግራጫ፣ ቲምበርዎልፍ፣ ማናቴ እና ካዴት ሰማያዊ ናቸው። እ.ኤ.አ. በ 1990 ክሪዮላ የመጀመሪያው ግራጫ ቀለም ጡረታ ወጣ ፣ እና ሰማያዊ ግራጫ ከ 7 ሌሎች ቀለሞች ጋር ጥቅም መስጠት አቁመው ተቋረጡ።

ይኽን ግራጫ ቀለም በብዛት ተፈጥሮ እምውስጥ እናገኘዋለን ዶልፊን ፣ አሳ ነባሪ ፣ ቀበሮ እና ሌሌች በርካታ እንስሳት ይኽን ግራጫ ቀለም ሲይዙ በጫካ የሚኖሩ ወፎችም ይኽ ቀለም እለታ ይውልላቸዋል ትናንሽ የጫካ ወፎችን ከጥቃት ሰውሮ የሚደብቀው ግራጫ ቀለም ነው።

ግራጫ ቃላት፣ ሀረጎች እና ምሳሌያዊ ፈሊጦች

የግራጫ ትርጉም በቋንቋዎች ውስጥ እንዴት እንደሚገለጽ  ምሳሌዎች፡-እንይ

ግራጫ ገበያ (Gray market) :- ከሚታወቀው በታች ዋጋ ያላቸውን ዕቃዎች የመግዛት ወይም የመሸጥ ሥራ።

ግራጫ ስሜት: (Gray mood ) :- ደስተኛ ያልሆነ ስሜት

ግራጫ አካባቢ፡ (Gray area) :- በሁለት የተለያዩ እይታዎች መካከል የተያዘ

ስለ ግራጫ ቀለም ጥቅሶች

"የእውነት ቀለም ግራጫ ነው"

አንድሬ ጊዴ፣ ፈረንሳዊ ደራሲ እና የኖቤል ሽልማት አሸናፊ፣ እኤአ 1869-1951

የሥዕሌት ሁሉ ጠላት ግራጫ መሆኑን አስታውስ ! በብርሃን ሥር ባለው ሥፍራ ምክንያት ፣ ሥዕል ሁልጊዜ ማለት ይቻላል ግራጫማ ሆኖ ይታያል፣

ዩጂን ዴላክሮክስ፣ እኤአ ከ 1798-1863 የፈረንሳይ ሮማንቲክ ዘመን መሪ አርቲስቶች አንዱ።

" ከአብረቅራቂ ይልቅ ግራጫ ይሻላል"

ዣን ኦገስት-ዶሚኒክ ፣ ፈረንሳዊው ኒዮክላሲካል ሰዓሊ፣ 1780-1867

"ግራጫ ቀን ምርጥ ብርሃን ይሰጣል"

ሊዮናርዶ ዳ ቪንቺ, የጣሊያን ፖሊማት እና ሰዓሊ, 1452-1519

ግራጫ ፣ ከሁሉም በጣም አስፈላጊው ቀለም ነው፣ የአመለካከት አለመኖር ፣ ምንምነት  -

ገርሃርድ ሪችተር የጀርመን ቪዥዋል አርቲስት

ጌቶቹን የሚለየው መሠረታዊው ግራጫ ፣ ቀለማትን ይገልፃል እና የሁሉም ቀለሞች ነፍስ ነው።

ኦዲሎን ሬዶን ፣ የፈረንሣይ ተምሳሌት ሰዓሊ ፣ 1840-1916

ኃይለኛ ቀለም ወሰድክ ግራጫ ሳታደርግ ፣ ከጎኑ ኃይለኛ ማሟያ ካስቀመጥክ በጣም ሞቃት ነው ፣ ግራጫው ዓይን ምስላዊ ድብልቅን እንዲሠራ ያስችለዋል።

ሲሚ ኖክስ አሜሪካዊ ሰዓሊ፣ ለ. በ1935 ዓ.ም

ሁሉንም ነገር በግራጫ ውስጥ ካየሁ ፣ እና እኔ ያጋጠሙኝ እና እንደገና ማራባት የምፈልገውን ሁሉንም ቀለሞች በግራጫ ውስጥ ካየሁ ፣ ከዚያ ሌላ ማንኛውንም ቀለም ለምን እጠቀማለሁ? ይህን ለማድረግ ሞከርኩኝ፣ ምክንያቱም ከግራጫ ጋር ብቻ ለመሳል አላማዬ አልነበረም። ነገር ግን በስራዬ ውስጥ አንዱን ቀለም ከሌላው በኋላ አስወግዳለሁ፣  እና የቀረው ግራጫ ፣ ግራጫ ፣ ግራጫ ነው!

አልቤርቶ ጂያኮሜትቲ፣ የስዊዘርላንድ ቀራጭ፣ ሰዓሊ፣ ንድፍ አውጪ እና አታሚ፣ 1901-1966

ወራቶች በቀለማት ከተለዩ በኒው ኢንግላንድ ኖቬምበር ግራጫ ቀለም ይኖረዋል.

ማዴሊን ኩኒን፣ አሜሪካዊ ዲፕሎማት እና ፖለቲከኛ፣ ለ. በ1933 ዓ.ም

ኮንክሪት (ግራጫ ) በመሠረቱ ፣ የመጥፎ የአየር ሁኔታ ቀለም ነው.

ዊልያም ዲን ሃሚልተን, አሜሪካዊ ደራሲ

ግራጫ በጣም ታላቅ ነው ፣ ሰዎች ግራጫ ገለልተኛ ነው ብለው ያስባሉ፣ ግን እኔ እንደማስበው ይህ ስሜት የሚነካ፣ ኃይለኛ፣ ድራማዊ እና ስሜታዊ (Sexy color) ነው። በጣም ስስ ነው።

ብራያን ባት፣ አሜሪካዊ ተዋናይ፣ ለ. በ1963 ዓ.ም

ግራጫ እንደ መታወቂያ ወይም መለያ ቀለም

የመለያ ቀለም ከተወዳጅ ቀለም የተለየ ነው ፣ ምንም እንኳን ለአንዳንድ ሰዎች ቀለማት አንድ እና ተመሳሳይ ቢሆኑም።
  በቀለም እራስዎን እንዴት እንደሚገልጹ ፣ እና እንዴት ያለማቋረጥ እንደሚለብሱ ወይም እራስዎን በቀለም መከበብዎ መለያዎ ያደርገዋል።

• አልበርት አንስታይን - ታዋቂው የፊዚክስ ሊቅ በየቀኑ ጠዋት ልብስ በመምረጥ የአዕምሮ ጉልበት ማባከን ስላልፈለገ ግራጫ ሱፍ ልብሶችን ብቻ ይለብስ እንደነበር ተዘግቧል።

• ማርክ ዙከርበርግ - የፌስቡክ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሁሌም ግራጫማ ቲሸርት ይለብሳል።

• ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ - የኋይት ሀውስ ቁም ሣጥኑን በግራጫ እና ሰማያዊ ልብሶች ብቻ ሞልቶታል ይላሉ።

Companies & Brands Identified by Gray

• Lexus

• Wikipedia

• Nissan

• Forbes

• Mercedes

Loading comments...